መዝሙር 28:1-9

  • የመዝሙራዊው ጸሎት ተሰሚነት አገኘ

    • ‘“ይሖዋ ብርታቴና ጋሻዬ ነው” (7)

የዳዊት መዝሙር። 28  ዓለቴ ይሖዋ ሆይ፣ ሁልጊዜ ወደ አንተ እጣራለሁ፤+አንተም ጆሮ አትንፈገኝ። ዝም ካልከኝ፣ወደ ጉድጓድ* እንደሚወርዱ ሰዎች እሆናለሁ።+   ወደ መቅደስህ ውስጠኛ ክፍል እጆቼን አንስቼ፣እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ በምጮኽበት ጊዜ ልመናዬን ስማ።+   ከክፉዎችና መጥፎ ነገር ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ጎትተህ አትውሰደኝ፤+እነሱ በልባቸው ክፋት እያለ ከባልንጀሮቻቸው ጋር የሰላም ቃል የሚያወሩ ናቸው።+   ለሠሩት ሥራ፣እንደ ክፉ ልማዳቸው ክፈላቸው።+ ለእጃቸው ሥራ መልሰህ ክፈላቸው፤እንዳደረጉትም መልስላቸው።+   ይሖዋ ላከናወናቸው ነገሮች፣ለእጆቹም ሥራ ትኩረት አይሰጡምና።+ እሱ ያፈርሳቸዋል፤ ደግሞም አይገነባቸውም።   እርዳታ ለማግኘት ያቀረብኩትን ልመና ስለሰማይሖዋ የተመሰገነ ይሁን።   ይሖዋ ብርታቴና+ ጋሻዬ ነው፤+ልቤ በእሱ ይተማመናል።+ ከእሱ እርዳታ ስላገኘሁ ልቤ ሐሴት ያደርጋል፤በመዝሙሬም አወድሰዋለሁ።   ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ነው፤ለቀባው ታላቅ መዳን የሚያስገኝ መሸሸጊያ ነው።+   ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ።+ ለዘላለም እረኛ ሁናቸው፤ በክንድህም ተሸከማቸው።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “መቃብር።”