መዝሙር 29:1-11
የዳዊት ማህሌት።
29 እናንተ የኃያላን ልጆች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ።+
2 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለይሖዋ ስጡ።
ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ* ለይሖዋ ስገዱ።*
3 የይሖዋ ድምፅ ከውኃዎች በላይ ተሰማ፤ክብር የተጎናጸፈው አምላክ አንጎደጎደ።+
ይሖዋ ከብዙ ውኃዎች በላይ ነው።+
4 የይሖዋ ድምፅ ኃይለኛ ነው፤+የይሖዋ ድምፅ ክብራማ ነው።
5 የይሖዋ ድምፅ አርዘ ሊባኖስን ይሰብራል፤አዎ፣ ይሖዋ አርዘ ሊባኖስን ይሰባብራል።+
6 ሊባኖስን* እንደ ጥጃ፣ሲሪዮንንም+ እንደ ዱር በሬ እንቦሳ እንዲዘሉ ያደርጋል።
7 የይሖዋ ድምፅ የእሳት ነበልባል ይረጫል፤+
8 የይሖዋ ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤+ይሖዋ የቃዴስን+ ምድረ በዳ ያናውጣል።
9 የይሖዋ ድምፅ ርኤሞች* እንዲርበተበቱና እንዲወልዱ ያደርጋል፤ደኖችንም ያራቁታል።+
በቤተ መቅደሱም ውስጥ ያሉ ሁሉ “ክብር ለአምላክ!” ይላሉ።
10 ይሖዋ ከሚያጥለቀልቁት ውኃዎች*+ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ይሖዋ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ በዙፋን ላይ ይቀመጣል።+
11 ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ይሰጣል።+
ይሖዋ ሰላም በመስጠት ሕዝቡን ይባርካል።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ “ከቅድስናው ግርማ የተነሳ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “ይሖዋን አምልኩ።”
^ የሊባኖስን ሰንሰለታማ ተራሮች የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
^ ቅርንጫፍ የሚመስሉ ቀንዶች ያሉት አጥቢ እንስሳ፤ ከአጋዘን ጋር ይመሳሰላል።
^ ወይም “በሰማይ ካለው ውቅያኖስ።”