መዝሙር 99:1-9

  • ቅዱስ ንጉሥ የሆነው ይሖዋ

    • ዙፋኑ ከኪሩቤል በላይ ነው (1)

    • ይቅር የሚልና የሚቀጣ አምላክ (8)

99  ይሖዋ ነገሠ።+ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ። እሱ ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን ተቀምጧል።+ ምድር ትናወጥ።   ይሖዋ በጽዮን ታላቅ ነው፤ከሕዝቦችም ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው።+   ሕዝቦች ታላቅ ስምህን ያወድሱ፤+ስምህ እጅግ የሚፈራና ቅዱስ ነውና።   እሱ ፍትሕን የሚወድ ኃያል ንጉሥ ነው።+ አንተ ቅን የሆነውን ነገር በጽኑ መሥርተሃል። ፍትሕንና ጽድቅን ለያዕቆብ አስፍነሃል።+   ይሖዋ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፤+ በእግሩ ማሳረፊያ ፊት ስገዱ፤*+እሱ ቅዱስ ነው።+   ከካህናቱ መካከል ሙሴና አሮን ይገኙበታል፤+ስሙን ከሚጠሩ መካከልም ሳሙኤል አንዱ ነው።+ እነሱ ወደ ይሖዋ ይጣሩ ነበር፤እሱም ይመልስላቸው ነበር።+   በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ያነጋግራቸው ነበር።+ ማሳሰቢያዎቹንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠብቀዋል።+   አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ አንተ መልስ ሰጠሃቸው።+ ይቅር ባይ አምላክ ሆንክላቸው፤+ሆኖም ለሠሯቸው ኃጢአቶች ቀጣሃቸው።*+   አምላካችንን ይሖዋን ከፍ ከፍ አድርጉት፤+በቅዱስ ተራራውም+ ፊት ስገዱ፤*አምላካችን ይሖዋ ቅዱስ ነውና።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

“በኪሩቤል መካከል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “አምልኩ።”
ቃል በቃል “ተበቀልካቸው።”
ወይም “አምልኩ።”