መዝሙር 126:1-6

  • ጽዮን ወደ ቀድሞ ሁኔታዋ ተመለሰች

    • “ይሖዋ ታላላቅ ነገሮች አደረገልን” (3)

    • ለቅሷቸው ወደ ደስታ ይለወጣል (5, 6)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። 126  ይሖዋ የጽዮንን ምርኮኞች መልሶ በሰበሰበ ጊዜ፣+ሕልም የምናይ መስሎን ነበር።   በዚያን ጊዜ አፋችን በሳቅ፣አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ።+ ያን ጊዜ ብሔራት እንዲህ አሉ፦ “ይሖዋ ታላላቅ ነገሮች አደረገላቸው።”+   ይሖዋ ታላላቅ ነገሮች አደረገልን፤+እኛም እጅግ ተደሰትን።   ይሖዋ ሆይ፣ በኔጌብ እንዳሉ ጅረቶች፣*የተማረኩብንን ሰዎች መልሰህ ሰብስብ።*   በእንባ የሚዘሩ፣በእልልታ ያጭዳሉ።   ዘር ቋጥሮ የወጣው ሰው፣የሄደው እያለቀሰ ቢሆንም እንኳነዶውን ተሸክሞእልል እያለ ይመለሳል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በደቡብ እንዳሉ ደረቅ ወንዞች።”
ወይም “ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ መልስ።”