መዝሙር 47:1-9

  • አምላክ በመላው ምድር ላይ ነግሦአል

    • “ይሖዋ እጅግ የሚያስፈራ ነው” (2)

    • “ለአምላክ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ” (6, 7)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት። 47  እናንተ ሕዝቦች ሁሉ፣ እጆቻችሁን አጨብጭቡ። በድል አድራጊነት ለአምላክ እልል በሉ።   ልዑሉ ይሖዋ እጅግ የሚያስፈራ ነውና፤+በመላው ምድር ላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።+   ሕዝቦችን ለእኛ ያስገዛል፤ብሔራትም ከእግራችን በታች እንዲሆኑ ያደርጋል።+   የሚወደውን የያዕቆብን+ መመኪያርስታችን አድርጎ ይመርጥልናል።+ (ሴላ)   አምላክ በእልልታ አረገ፤ይሖዋ በቀንደ መለከት* ድምፅ ወደ ላይ ወጣ።   ለአምላክ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ። ለንጉሣችን የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።   አምላክ የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤+የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ ማስተዋልም ይኑራችሁ።   አምላክ በብሔራት ላይ ነግሦአል።+ በቅዱስ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል።   የሕዝቡ መሪዎች ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋርአንድ ላይ ተሰብስበዋል። የምድር ገዢዎች* የአምላክ ናቸውና። እሱ እጅግ ከፍ ከፍ ብሏል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በአውራ በግ ቀንድ፤ በትራምፔት።”
ቃል በቃል “ጋሻዎች።”