መዝሙር 137:1-9

  • በባቢሎን ወንዞች አጠገብ

    • የጽዮንን መዝሙሮች አልዘመሩም (3, 4)

    • ባቢሎን ትጠፋለች (8)

137  በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣+ በዚያ ተቀምጠን ነበር። ጽዮንን ባስታወስናት ጊዜ አለቀስን።+   በመካከሏ* በሚገኙ የአኻያ ዛፎች ላይበገናዎቻችንን ሰቀልን።+   የማረኩን ሰዎች በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤+የሚያፌዙብን ሰዎች በመዝሙር እንድናዝናናቸው “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን።   የይሖዋን መዝሙርበባዕድ ምድር እንዴት ልንዘምር እንችላለን?   ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አንቺን ብረሳ፣ቀኝ እጄ ትክዳኝ።*+   ሳላስታውስሽ ብቀር፣ኢየሩሳሌምን ለደስታዬ ምክንያትከሆኑት ነገሮች በላይ ባላደርግ፣+ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ትጣበቅ።   ይሖዋ ሆይ፣ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀንኤዶማውያን ያሉትን አስታውስ፤ “አፍርሷት! ከሥረ መሠረቷ አፍርሷት!”+ ብለው ነበር።   በቅርቡ የምትጠፊው አንቺ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣+በእኛ ላይ በፈጸምሽው በዚያው ድርጊትብድራትሽን የሚመልስ ደስተኛ ይሆናል።+   ልጆችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጥ+ደስተኛ ይሆናል።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ባቢሎንን ያመለክታል።
“ትመንምን” ማለትም ሊሆን ይችላል።