መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች
መጽሐፍ ቅዱሳዊ መጽሔቶቻችን የምልክት ቋንቋዎችን ጨምሮ በመቶዎች በሚቆጠሩ ቋንቋዎች ይገኛሉ። መጠበቂያ ግንብ መጽሔት ስለ አምላክ መንግሥት የሚገልጸውን ምሥራች በማብሰር ሰዎችን ያጽናናል፤ እንዲሁም ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ያበረታታል። ንቁ! መጽሔት የዘመናችንን ችግሮች እንዴት መቋቋም እንደምንችል ይጠቁመናል። ሰዎች፣ ፈጣሪ ሰላም የሰፈነበትና አስተማማኝ አዲስ ዓለም እንደሚያመጣ በሰጠው ተስፋ ላይ ያላቸውን እምነት እንዲያሳድጉ ይረዳል።

