መዝሙር 23:1-6

  • “ይሖዋ እረኛዬ ነው”

    • “የሚጎድልብኝ ነገር የለም” (1)

    • “ኃይሌን ያድሳል” (3)

    • “ጽዋዬ ጢም ብሎ ሞልቷል” (5)

የዳዊት ማህሌት። 23  ይሖዋ እረኛዬ ነው።+ የሚጎድልብኝ ነገር የለም።+   በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤ውኃ ወዳለበት የእረፍት ቦታም* ይመራኛል።+   ኃይሌን* ያድሳል።+ ለስሙ ሲል በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።+   ድቅድቅ ጨለማ በዋጠው ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ+አንተ ከእኔ ጋር ስለሆንክ፣+ጉዳት ይደርስብኛል ብዬ አልፈራም፤+በትርህና ምርኩዝህ ያበረታቱኛል።*   በጠላቶቼ ፊት ማዕድ አዘጋጀህልኝ።+ ራሴን በዘይት ቀባህ፤+ጽዋዬ ጢም ብሎ ሞልቷል።+   ጥሩነትህና ታማኝ ፍቅርህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፤+ዕድሜዬንም በሙሉ በይሖዋ ቤት እኖራለሁ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

“ወደ እረፍት ውኃዎች” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ነፍሴን።”
ወይም “ያጽናኑኛል።”