መዝሙር 150:1-6

  • እስትንፋስ ያለው ሁሉ ያህን ያወድስ

    • ሃሌሉያህ! (1, 6)

150  ያህን አወድሱ!*+ አምላክን በተቀደሰ ስፍራው አወድሱት።+ ብርታቱን በሚያሳየው ጠፈር* አወድሱት።+   ስለ ብርቱ ሥራዎቹ አወድሱት።+ ወደር የለሽ ስለሆነው ታላቅነቱ አወድሱት።+   በቀንደ መለከት+ ድምፅ አወድሱት። በባለ አውታር መሣሪያና በበገና አወድሱት።+   በአታሞና+ በሽብሸባ አወድሱት። በባለ አውታር መሣሪያና+ በዋሽንት+ አወድሱት።   በሚያስተጋባ ሲምባል* አወድሱት። ኃይለኛ ድምፅ በሚያወጣ ሲምባል+ አወድሱት።   እስትንፋስ ያለው ሁሉ ያህን ያወድስ። ያህን አወድሱ!*+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ወይም “ስለ ብርታቱ በሚመሠክረው ሰማይ።”
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል፣ እርስ በርሱ ሲጋጭ ኃይለኛ ድምፅ የሚያወጣን ክብ ቅርጽ ያለው ከብረት የተሠራ የሙዚቃ መሣሪያ ያመለክታል።
ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።