መዝሙር 21:1-13

  • በይሖዋ የሚታመነው ንጉሥ የሚያገኛቸው በረከቶች

    • ንጉሡ ረጅም ዕድሜ ተሰጠው (4)

    • የአምላክ ጠላቶች ድል ይደረጋሉ (8-12)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት። 21  ይሖዋ ሆይ፣ ንጉሡ በአንተ ብርታት ደስ ይለዋል፤+በማዳን ሥራህ እጅግ ሐሴት ያደርጋል!+   የልቡን ፍላጎት አሟልተህለታል፤+የከንፈሩንም ልመና አልከለከልከውም። (ሴላ)   የተትረፈረፉ በረከቶች ይዘህ ተቀበልከው፤ምርጥ ከሆነ* ወርቅ የተሠራ አክሊልም በራሱ ላይ ደፋህለት።+   ሕይወትን ለመነህ፤አንተም ረጅም ዕድሜ* ብሎም የዘላለም ሕይወት ሰጠኸው።+   የማዳን ሥራህ ታላቅ ክብር ያስገኝለታል።+ ሞገስና ግርማ አጎናጸፍከው።   ለዘላለም እንዲባረክ አደረግከው፤+ከእሱ ጋር እንዳለህ ሲያውቅ* በጣም ደስ ይለዋል።+   ንጉሡ በይሖዋ ይተማመናልና፤+በልዑሉ አምላክ ታማኝ ፍቅር የተነሳ ፈጽሞ አይናወጥም።*+   እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ይይዛቸዋል፤ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ይይዛቸዋል።   በተወሰነው ጊዜ ትኩረትህን በእነሱ ላይ ስታደርግ እሳት እንደሚንቀለቀልበት ምድጃ ታደርጋቸዋለህ። ይሖዋ በቁጣው ይውጣቸዋል፤ እሳትም ይበላቸዋል።+ 10  የሆዳቸውን ፍሬ ከምድር ገጽ፣ዘራቸውንም ከሰው ልጆች መካከል ታጠፋለህ። 11  በአንተ ላይ ክፉ ለመሥራት አስበዋልና፤+ሊሳካ የማይችል ሴራ ጠንስሰዋል።+ 12  ቀስትህን* በእነሱ ላይ* በማነጣጠርእንዲያፈገፍጉ ታደርጋለህና።+ 13  ይሖዋ ሆይ፣ በብርታትህ ተነስ። ለኃያልነትህ የውዳሴ መዝሙር እንዘምራለን።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ከጠራ።”
ቃል በቃል “የቀኖች ርዝማኔ።”
ቃል በቃል “በፊትህ ደስታ።”
ወይም “ፈጽሞ አይንገዳገድም (አይውተረተርም)።”
ቃል በቃል “የደጋንህን አውታር።”
ቃል በቃል “በፊታቸው።”