መዝሙር 123:1-4

  • የይሖዋን ሞገስ መሻት

    • ‘ወደ ይሖዋ እንመለከታለን’ (2)

    • “ንቀት እጅግ በዝቶብናል” (3)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። 123  በሰማያት ዙፋን ላይ የተቀመጥክ ሆይ፣ዓይኖቼን ወደ አንተ አነሳለሁ።+   የአገልጋዮች ዓይን ወደ ጌታቸው እጅ፣የሴት አገልጋይም ዓይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሚመለከት ሁሉ፣የእኛም ዓይኖች ሞገስ እስኪያሳየን ድረስ+ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመለከታሉ።+   ንቀት እጅግ በዝቶብናልና፣+ሞገስ አሳየን፤ ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየን።   ከልክ በላይ በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎችን ፌዝ፣የእብሪተኞችንም ንቀት ጠግበናል።*

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ነፍሳችን ከልክ በላይ ጠግባለች።”