መዝሙር 120:1-7

  • ሰላምን የናፈቀ የባዕድ አገር ሰው

    • “ከአታላይ አንደበት ታደገኝ” (2)

    • “እኔ ለሰላም ቆሜአለሁ” (7)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።* 120  በተጨነቅኩ ጊዜ ይሖዋን ተጣራሁ፤+እሱም መለሰልኝ።+   ይሖዋ ሆይ፣ ከሐሰተኛ ከንፈር፣ደግሞም ከአታላይ አንደበት ታደገኝ።*   አንተ አታላይ አንደበት፣አምላክ ምን ያደርግህ ይሆን? እንዴትስ ይቀጣህ ይሆን?*+   ሹል በሆኑ የተዋጊ ፍላጻዎችና+በክትክታ እንጨት ፍም+ ይቀጣሃል።   በመሼቅ+ የባዕድ አገር ሰው ሆኜ ስለኖርኩ ወዮልኝ! በቄዳር+ ድንኳኖች መካከል ኖሬአለሁ።   ሰላም ከሚጠሉ ሰዎች ጋርለረጅም ጊዜ ኖሬአለሁ።*+   እኔ ለሰላም ቆሜአለሁ፤እነሱ ግን በተናገርኩ ቁጥር ለጦርነት ይነሳሉ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ነፍሴን ታደጋት።”
ቃል በቃል “ደግሞስ ምን ይጨምርልህ ይሆን?”
ወይም “ነፍሴ ለረጅም ጊዜ ኖራለች።”