መዝሙር 148:1-14

  • ፍጥረት ሁሉ ይሖዋን ያወድስ

    • “መላእክቱ ሁሉ፣ አወድሱት” (2)

    • ‘ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት አወድሱት’ (3)

    • ወጣቶችና ሽማግሌዎች አምላክን አወድሱ (12, 13)

148  ያህን አወድሱ!* ይሖዋን ከሰማያት አወድሱት፤+በከፍታ ቦታዎች አወድሱት።   መላእክቱ ሁሉ፣ አወድሱት።+ ሠራዊቱ ሁሉ፣+ አወድሱት።   ፀሐይና ጨረቃ፣ አወድሱት። የምታብረቀርቁ ከዋክብት ሁሉ፣ አወድሱት።+   ሰማየ ሰማያት፣ አወድሱት፤ከሰማያት በላይ ያላችሁ ውኃዎች፣ አወድሱት።   የይሖዋን ስም ያወድሱ፤እሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና።+   ለዘላለም አጸናቸው፤+ጊዜ የማይሽረው ድንጋጌ አውጥቷል።+   ይሖዋን ከምድር አወድሱት፤እናንተ ግዙፍ የባሕር ፍጥረታትና ጥልቅ ውኃዎች ሁሉ፣   መብረቅና በረዶ፣ አመዳይና ጥቅጥቅ ያለ ደመና፣አንተም ቃሉን የምትፈጽም አውሎ ነፋስ፣+   እናንተ ተራሮችና ኮረብቶች ሁሉ፣+እናንተ ፍሬ የምታፈሩ ዛፎችና አርዘ ሊባኖሶች ሁሉ፣+ 10  እናንተ የዱር እንስሳትና+ የቤት እንስሳት ሁሉ፣እናንተ መሬት ለመሬት የምትሳቡ ፍጥረታትና ክንፍ ያላችሁ ወፎች፣ 11  እናንተ የምድር ነገሥታትና ብሔራት ሁሉ፣እናንተ መኳንንትና የምድር ፈራጆች ሁሉ፣+ 12  እናንተ ወጣት ወንዶችና ወጣት ሴቶች፣*ሽማግሌዎችና ልጆች በኅብረት አወድሱት። 13  የይሖዋን ስም ያወድሱ፤ስሙ ብቻውን ከሌሎች ሁሉ በላይ ነውና።+ ግርማው ከምድርና ከሰማይ በላይ ነው።+ 14  ታማኝ አገልጋዮቹ ሁሉ፣ማለትም ለእሱ ቅርብ የሆኑት የሕዝቡ የእስራኤል ልጆች ይወደሱ ዘንድየሕዝቡን ብርታት* ከፍ ያደርጋል። ያህን አወድሱ!*

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ቃል በቃል “ደናግል።”
ቃል በቃል “ቀንድ።”
ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።