መዝሙር 7:1-17

  • ይሖዋ ጻድቅ ፈራጅ ነው

    • ‘ይሖዋ ሆይ፣ ፍረድልኝ’ (8)

ቢንያማዊው ኩሽ የተናገረውን ቃል በተመለከተ ዳዊት ለይሖዋ ያንጎራጎረው ሙሾ።* 7  አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ።+ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ፤ ታደገኝም።+   አለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል፤*+የሚታደገኝ በሌለበት ነጥቀው ይወስዱኛል።   አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ የሠራሁት አንዳች ጥፋት ካለ፣አግባብ ያልሆነ ድርጊት ፈጽሜ ከሆነ፣   መልካም ያደረገልኝን ሰው በድዬ ከሆነ፣+ወይም ያላንዳች ምክንያት ጠላቴን ዘርፌ ከሆነ፣*   ጠላት አሳዶ ይያዘኝ፤*ሕይወቴን መሬት ላይ ይጨፍልቃት፤ክብሬንም ከአፈር ይደባልቀው። (ሴላ)   ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ ተነስ፤በእኔ ላይ በቁጣ በሚገነፍሉት ጠላቶቼ ላይ ተነስ፤+ለእኔ ስትል ንቃ፤ ፍትሕ እንዲሰፍንም እዘዝ።+   ብሔራት ይክበቡህ፤አንተም ከላይ ሆነህ በእነሱ ላይ እርምጃ ትወስዳለህ።   ይሖዋ በሕዝቦች ላይ ፍርድ ያስተላልፋል።+ ይሖዋ ሆይ፣ እንደ ጽድቄ፣እንደ ንጹሕ አቋሜም* ፍረድልኝ።+   እባክህ፣ የክፉ ሰዎች ክፋት እንዲያከትም አድርግ። ጻድቁን ሰው ግን አጽና፤+ልብንና+ ጥልቅ ስሜትን የምትመረምር*+ ጻድቅ አምላክ ነህና።+ 10  ቀና ልብ ያላቸውን ሰዎች የሚያድነው+ አምላክ ጋሻዬ ነው።+ 11  አምላክ ጻድቅ ፈራጅ ነው፤+በየቀኑም ፍርዱን ያውጃል።* 12  ማንም ሰው ንስሐ የማይገባ ከሆነ፣+ አምላክ ሰይፉን ይስላል፤+ደጋኑን ወጥሮ ያነጣጥራል።+ 13  ገዳይ የሆኑ መሣሪያዎቹን ያሰናዳል፤የሚንበለበሉ ፍላጻዎቹን ያዘጋጃል።+ 14  ክፋትን ያረገዘውን ሰው ተመልከት፤ችግርን ይፀንሳል፤ ሐሰትንም ይወልዳል።+ 15  ጉድጓድ ይምሳል፤ ጥልቅ አድርጎም ይቆፍረዋል፤ሆኖም በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ራሱ ይወድቃል።+ 16  የሚያመጣው ችግር በራሱ ላይ ይመለሳል፤+የዓመፅ ድርጊቱ በገዛ አናቱ ላይ ይወርዳል። 17  ይሖዋን ለፍትሑ አወድሰዋለሁ፤+ለልዑሉ አምላክ+ ለይሖዋ ስም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ።”
ወይም “ነፍሴን ይዘነጣጥሏታል።”
“ያለምክንያት የሚቃወመኝን ሰው ትቼ፣ መልካም ያደረገልኝን ሰው በድዬ ከሆነ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ነፍሴን አሳዶ ይያዛት።”
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል የሥነ ምግባር ንጽሕናን፣ ሁለት ልብ አለመሆንንና እንከን የለሽ መሆንን ያመለክታል።
ወይም “ልብንና ኩላሊትን የምትፈትን።”
ወይም “የውግዘት ቃላት ይሰነዝራል።”