መዝሙር 2:1-12

  • ይሖዋና እሱ የቀባው ንጉሥ

    • ይሖዋ በብሔራት ላይ ይስቃል (4)

    • ይሖዋ ንጉሡን ይሾማል (6)

    • ልጁን አክብሩ (12)

2  ብሔራት የታወኩት ለምንድን ነው?ሕዝቦችስ ከንቱ ነገር የሚያጉተመትሙት* ለምንድን ነው?+   የምድር ነገሥታት ተሰለፉ፤ከፍተኛ ባለሥልጣናትም በአንድነት ተሰብስበው*+በይሖዋና እሱ በቀባው ላይ*+ ተነሱ።   “ሰንሰለታቸውን እንበጥስ፤ገመዳቸውንም እናስወግድ!” ይላሉ።   በሰማያት በዙፋን ላይ የተቀመጠው ይስቃል፤ይሖዋ ይሳለቅባቸዋል።   በዚያን ጊዜ በቁጣ ይናገራቸዋል፤በሚነድ ቁጣውም ያሸብራቸዋል፤   እንዲህም ይላቸዋል፦ “እኔ ራሴ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን+ ላይንጉሤን ሾምኩ።”+   የይሖዋን ድንጋጌ ልናገር፤እንዲህ ብሎኛል፦ “አንተ ልጄ ነህ፤+እኔ ዛሬ ወለድኩህ።+   ጠይቀኝ፤ ብሔራትን ርስትህ፣የምድርንም ዳርቻዎች ግዛትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ።+   በብረት በትረ መንግሥት ትሰብራቸዋለህ፤+እንደ ሸክላ ዕቃም ታደቃቸዋለህ።”+ 10  እንግዲህ እናንተ ነገሥታት አስተውሉ፤እናንተ የምድር ፈራጆች እርማት ተቀበሉ።* 11  ይሖዋን በፍርሃት አገልግሉ፤ለእሱ በመንቀጥቀጥም ሐሴት አድርጉ። 12  ልጁን አክብሩ፤*+ አለዚያ አምላክ* ይቆጣል፤ከመንገዱም ትጠፋላችሁ፤+ቁጣው ፈጥኖ ይነድዳልና። እሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ደስተኞች ናቸው።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “የሚያውጠነጥኑት።”
ወይም “ተማክረው።”
ወይም “በእሱ ክርስቶስ ላይ።”
ወይም “ተጠንቀቁ።”
ቃል በቃል “ሳሙት።”
ቃል በቃል “እሱ።”