መዝሙር 114:1-8

  • እስራኤል ከግብፅ ወጣ

    • ባሕሩ ሸሸ (5)

    • ተራሮች እንደ አውራ በግ ዘለሉ (6)

    • ጠንካራውን ዓለት ወደ ውኃ ምንጮች ይለውጣል (8)

114  እስራኤል ከግብፅ ሲወጣ፣+የያዕቆብ ቤት ባዕድ ቋንቋ ከሚናገር ሕዝብ ተለይቶ ሲሄድ፣  2  ይሁዳ መቅደሱ፣*እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።+  3  ባሕሩ ይህን አይቶ ሸሸ፤+ዮርዳኖስ ወደ ኋላ ተመለሰ።+  4  ተራሮች እንደ አውራ በግ፣ኮረብቶች እንደ ጠቦት ፈነጩ።+  5  አንተ ባሕር ሆይ፣ የሸሸኸው ምን ሆነህ ነው?+ ዮርዳኖስ ሆይ፣ ወደ ኋላ የተመለስከው ለምንድን ነው?+  6  ተራሮች ሆይ፣ እንደ አውራ በግ የዘለላችሁት፣እናንተ ኮረብቶች፣ እንደ ጠቦት የፈነጫችሁት ለምንድን ነው?  7  ምድር ሆይ፣ ከጌታ የተነሳ፣ከያዕቆብም አምላክ የተነሳ ተንቀጥቀጪ፤+  8  እሱ ዓለቱን ቄጠማ ወደሞላበት ኩሬ፣ጠንካራውንም ዓለት ወደ ውኃ ምንጮች ይለውጣል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ቅዱስ ስፍራው።”