ጥያቄ 14
ያሉህን ነገሮች በጥበብ መጠቀም የምትችለው እንዴት ነው?
“ፈንጠዝያ የሚወድ ሰው ይደኸያል፤ የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድ ባለጸጋ አይሆንም።”
“ተበዳሪም የአበዳሪው ባሪያ ነው።”
“ከእናንተ መካከል፣ ግንብ ለመገንባት ፈልጎ ለመጨረስ የሚያስችል በቂ ገንዘብ እንዳለው ለማወቅ በመጀመሪያ ተቀምጦ ወጪውን የማያሰላ ማን ነው? እንዲህ ካላደረገ ግን መሠረቱን ከጣለ በኋላ ፍጻሜ ላይ ማድረስ ሊያቅተውና የሚያዩት ሰዎች ሁሉ ሊያፌዙበት ይችላሉ፤ ‘ይህ ሰው መገንባት ጀምሮ ነበር፤ መጨረስ ግን አቃተው’ ይሉታል።”
“በልተው ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን ‘ምንም እንዳይባክን የተረፈውን ቁርስራሽ ሁሉ ሰብስቡ’ አላቸው።”