መዝሙር 41:1-13

  • የታመመ ሰው ጸሎት

    • አምላክ የታመመውን ይደግፈዋል (3)

    • የቅርብ ወዳጁ ከዳው (9)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት። 41  ለተቸገረ ሰው የሚያስብ ደስተኛ ነው፤+በመከራ ቀን ይሖዋ ይታደገዋል።   ይሖዋ ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል። በምድር ላይ ደስተኛ ይባላል፤+ለጠላቶቹ ምኞት* አሳልፈህ አትሰጠውም።+   ታሞ በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ ይሖዋ ይደግፈዋል፤+በታመመበት ወቅት መኝታውን ሙሉ በሙሉ ትቀይርለታለህ።   እኔም “ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ።+ በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና+ ፈውሰኝ”*+ አልኩ።   ጠላቶቼ ግን “የሚሞተውና ስሙ ከናካቴው የሚረሳው መቼ ነው?” እያሉ ስለ እኔ ክፉ ወሬ ያወራሉ።   ከእነሱ አንዱ እኔን ለማየት ቢመጣ ልቡ ውሸት ይናገራል። እኔን የሚጎዳ ወሬ ይቃርማል፤ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ በየቦታው ያወራዋል።   የሚጠሉኝ ሁሉ እርስ በርስ ይንሾካሾካሉ፤በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይሸርባሉ፤   “ክፉ ነገር ደርሶበታል፤ከእንግዲህ ከወደቀበት አይነሳም” ይላሉ።+   ሌላው ቀርቶ ከእኔ ጋር ሰላም የነበረው፣ እምነት የጣልኩበትና+ከማዕዴ ይበላ የነበረ ሰው ተረከዙን በእኔ ላይ አነሳ።*+ 10  ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ብድራታቸውን እከፍል ዘንድሞገስ አሳየኝ፤ ደግሞም አንሳኝ። 11  ጠላቴ በእኔ ላይ በድል አድራጊነት እልል ሳይል ሲቀር፣ አንተ በእኔ ደስ እንደተሰኘህ በዚህ አውቃለሁ።+ 12  እኔ በበኩሌ ንጹሕ አቋሜን* በመጠበቄ ትደግፈኛለህ፤+በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ።+ 13  የእስራኤል አምላክ ይሖዋከዘላለም እስከ ዘላለም ይወደስ።+ አሜን፣ አሜን።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ፍላጎት፤ ነፍስ።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ነፍሴን ፈውሳት።”
ወይም “እኔን ለማጥቃት ተነሳ።”
መዝ 7:8 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።