በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥያቄ 2

ስለ አምላክ ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?

 “ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ በውስጡ የተጻፈውንም በጥንቃቄ መፈጸም እንድትችል ቀንም ሆነ ሌሊት በለሆሳስ አንብበው፤ እንዲህ ካደረግክ መንገድህ ይቃናልሃል፤ እንዲሁም ማንኛውንም ነገር በጥበብ ማከናወን ትችላለህ።”

ኢያሱ 1:8

 “እነሱም ከመጽሐፉ ይኸውም ከእውነተኛው አምላክ ሕግ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በማንበብ ሕጉን በግልጽ ያብራሩና ትርጉሙ ምን እንደሆነ ይናገሩ ነበር፤ በዚህ መንገድ የተነበበውን ነገር ማስተዋል እንዲችል ሕዝቡን ይረዱት ነበር።”

ነህምያ 8:8

 “በክፉዎች ምክር የማይሄድ . . . ሰው ደስተኛ ነው። ይልቁንም በይሖዋ ሕግ ደስ ይለዋል፤ ሕጉንም በቀንና በሌሊት በለሆሳስ ያነበዋል። . . . የሚሠራውም ሁሉ ይሳካለታል።”

መዝሙር 1:1-3

 “ፊልጶስ ከሠረገላው ጎን እየሮጠ ጃንደረባው የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሐፍ ጮክ ብሎ ሲያነብ ሰማና ‘ለመሆኑ የምታነበውን ትረዳዋለህ?’ አለው። እሱም ‘የሚመራኝ ሰው ሳይኖር እንዴት ልረዳው እችላለሁ?’ አለው።”

የሐዋርያት ሥራ 8:30, 31

 “የማይታዩት ባሕርያቱ ይኸውም ዘላለማዊ ኃይሉና አምላክነቱ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ በግልጽ ይታያሉ፤ ምክንያቱም ባሕርያቱን ከተሠሩት ነገሮች ማስተዋል ይቻላል፤ ስለሆነም የሚያመካኙበት ነገር የላቸውም።”

ሮም 1:20

 “እድገትህ በሁሉም ሰዎች ዘንድ በግልጽ እንዲታይ በእነዚህ ነገሮች ላይ አሰላስል፤ እንዲሁም ትኩረትህ ሙሉ በሙሉ በእነዚህ ነገሮች ላይ ያረፈ ይሁን።”

1 ጢሞቴዎስ 4:15

 “እርስ በርስ ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች መነቃቃት እንድንችል አንዳችን ለሌላው ትኩረት እንስጥ፤ . . . መሰብሰባችንን ቸል አንበል።”

ዕብራውያን 10:24, 25

 “ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ሰው ካለ አምላክን ያለማሰለስ ይለምን፤ አምላክ ማንንም ሳይነቅፍ ለሁሉም በልግስና ይሰጣልና፤ ይህም ሰው ይሰጠዋል።”

ያዕቆብ 1:5