መዝሙር 27:1-14
የዳዊት መዝሙር።
27 ይሖዋ ብርሃኔና+ አዳኜ ነው።
ማንን እፈራለሁ?+
ይሖዋ የሕይወቴ ተገን ነው።+
ማን ያሸብረኛል?
2 ክፉዎች ሥጋዬን ለመብላት ባጠቁኝ ጊዜ፣+ተሰናክለው የወደቁት ባላጋራዎቼና ጠላቶቼ ናቸው።
3 ሠራዊት በዙሪያዬ ቢሰፍርም፣ልቤ በፍርሃት አይዋጥም።+
ጦርነት ቢከፈትብኝም እንኳበልበ ሙሉነት እመላለሳለሁ።
4 ይሖዋን አንድ ነገር ለመንኩት፤ምኞቴም ይኸው ነው፦በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በይሖዋ ቤት እኖር ዘንድ፣+ይሖዋ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን በትኩረት እመለከት ዘንድ፣ቤተ መቅደሱንም በአድናቆት አይ* ዘንድ ነው።+
5 በመዓት ቀን በመጠለያው ይሸሽገኛል፤+ሚስጥራዊ ቦታ በሆነው ድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛል፤+ከፍ ባለ ዓለት ላይ ያስቀምጠኛል።+
6 በመሆኑም ራሴ በዙሪያዬ ካሉ ጠላቶቼ በላይ ከፍ ብሏል፤በድንኳኑ ውስጥ በእልልታ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።
7 ይሖዋ ሆይ፣ በምጮኽበት ጊዜ ስማኝ፤+ሞገስ አሳየኝ፤ መልስም ስጠኝ።+
8 ልቤ በአንተ ቦታ ሆኖ ሲናገር
“ፊቴን ፈልጉ” ብሏል።
ይሖዋ ሆይ፣ ፊትህን እሻለሁ።+
9 ፊትህን ከእኔ አትሰውር።+
አገልጋይህን ተቆጥተህ ፊት አትንሳው።
አንተ ረዳቴ ነህ፤+አዳኝ አምላኬ ሆይ፣ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም።
10 የገዛ አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳ+ይሖዋ ራሱ ይቀበለኛል።+
11 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ፤+ከጠላቶቼ ጥበቃ እንዳገኝ ቀና በሆነ መንገድ ምራኝ።
12 ለጠላቶቼ* አሳልፈህ አትስጠኝ፤+ሐሰተኛ ምሥክሮች በእኔ ላይ ተነስተዋልና፤+ደግሞም እኔን ለማጥቃት ይዝቱብኛል።
13 በሕያዋን ምድር የይሖዋን ጥሩነት አያለሁ የሚል እምነት ባይኖረኝ ኖሮምን ይውጠኝ ነበር!*+
14 ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤+ደፋር ሁን፤ ልብህም ይጽና።+
አዎ፣ ይሖዋን ተስፋ አድርግ።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “በተመስጦ እመለከት።”
^ ወይም “ለጠላቶቼ ነፍስ።”
^ “በሕያዋን ምድር የይሖዋን ጥሩነት አያለሁ የሚል ጽኑ እምነት አለኝ” ማለትም ሊሆን ይችላል።