በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ስለ ይሖዋ ምሥክሮች

በአደባባይ ስንሰብክ አይተኸን ታውቅ ይሆናል። ስለ እኛ የተጻፉ የዜና ዘገባዎችን አንብበህ ወይም ሌሎች የሚሉትን ነገር ሰምተህ ሊሆን ይችላል። ያም ቢሆን ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ምን ያህል በትክክል ታውቃለህ?

በተጨማሪም፦ የይሖዋ ምሥክሮች ምን ብለው ያምናሉ?

የምናምንባቸው ነገሮች እና እንቅስቃሴዎቻችን

ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች

እኛን በተመለከተ ለሚፈጠሩብህ ጥያቄዎች በዚህ ገጽ ላይ መልስ ማግኘት ትችላለህ።

የይሖዋ ምሥክሮች ተሞክሮዎች

የይሖዋ ምሥክሮች አስተሳሰባቸው፣ ንግግራቸውና ምግባራቸው የአምላክ ቃል ከሆነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚስማማ እንዲሆን አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ያደርጋሉ።

የይሖዋ ምሥክሮች እንቅስቃሴ

ከ230 በላይ በሆኑ አገሮች ውስጥ የምንኖር ሲሆን የተለያየ አስተዳደግና ባሕል አለን። በስብከቱ ሥራችን በስፋት ብንታወቅም ኅብረተሰቡን የሚጠቅሙ ሌሎች ሥራዎችም እናከናውናለን።

በዓለም ዙሪያ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች

ስለ ዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበራችን የሚገልጹ አንዳንድ መረጃዎችን ተመልከት።

ነፃ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራም

መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለሚያሳስቧቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። አንተስ ለጥያቄዎችህ መልስ ማግኘት ትፈልጋለህ?

መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ ሰዎችን በነፃ መጽሐፍ ቅዱስን በማስተማራቸው ይታወቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስተምሩበት ፕሮግራም የሚካሄደው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

አንድ የይሖዋ ምሥክር እንዲያነጋግርህ ጠይቅ

ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ስለምትፈልገው የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሰ ጉዳይ መወያየት ወይም መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ ከምናስተምርበት ዝግጅት መጠቀም ትችላለህ።

ስብሰባዎች እና ዝግጅቶች

በስብሰባ አዳራሻችን ውስጥ ምን ይከናወናል?

አንተው ራስህ እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።

የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት

የት እንደምንሰበሰብና የአምልኮ ሥርዓታችን ምን እንደሚመስል ለማወቅ ይህን ገጽ ተመልከት። ስብሰባዎቻችን ለሁሉም ሰው ክፍት ናቸው፤ መዋጮም አይሰበሰብም።

የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ በዓል ለማክበር በየዓመቱ ይሰበሰባሉ። የኢየሱስ ሞት አንተን የሚጠቅመው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ እንድትገኝ በአክብሮት ተጋብዘሃል።

ቅርንጫፍ ቢሮዎች

ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ለመገናኘት

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችን አድራሻ።

የቤቴል ጉብኝት

በአቅራቢያህ የሚገኝን ቅርንጫፍ ቢሮ የጉብኝት ፕሮግራም ተመልከት።

የይሖዋ ምሥክሮች ለሥራቸው የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ የሚያገኙት እንዴት ነው?

ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚጠቀሙባቸውን ዘዴዎች አንጠቀምም።

በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?

የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሲሆን የተለያየ ዘር፣ ባሕልና አስተዳደግ ያላቸው ሰዎች ናቸው። እነዚህን ሰዎች አንድ ያደረጋቸው ምንድን ነው?

አጭር መረጃ​—በዓለም ዙሪያ

  • የይሖዋ ምሥክሮች የሚሰብኩባቸው አገሮች​—240

  • የይሖዋ ምሥክሮች​—8,695,808

  • መጽሐፍ ቅዱስን የሚማሩ ሰዎች​—7,705,765

  • በዓመታዊው የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ የተገኙ ሰዎች​—17,844,773

  • ጉባኤዎች​—120,387