መዝሙር 111:1-10

  • ለታላላቅ ሥራዎቹ ይሖዋን አወድሱ

    • የአምላክ ስም ቅዱስና እጅግ የሚፈራ ነው (9)

    • ይሖዋን መፍራት ጥበብ ነው (10)

111  ያህን አወድሱ!*+ א [አሌፍ] ቅኖች በተሰበሰቡበት ማኅበርና በጉባኤב [ቤት] ይሖዋን በሙሉ ልቤ አወድሰዋለሁ።+ ג [ጊሜል]   የይሖዋ ሥራ ታላቅ ነው፤+ד [ዳሌት] በሥራው የሚደሰቱ ሰዎች ሁሉ ያጠኑታል።+ ה []   ሥራው ግርማና ውበት የተላበሰ ነው፤ו [ዋው] ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+ ז [ዛየን]   አስደናቂ ሥራዎቹ እንዲታወሱ ያደርጋል።+ ח [ኼት] ይሖዋ ሩኅሩኅና* መሐሪ ነው።+ ט [ቴት]   ለሚፈሩት ምግብ ይሰጣል።+ י [ዮድ] ቃል ኪዳኑን ለዘላለም ያስታውሳል።+ כ [ካፍ]   የብሔራትን ርስት በመስጠት፣+ל [ላሜድ] ኃያል ሥራዎቹን ለሕዝቡ ገልጧል። ס [ሜም]   የእጆቹ ሥራዎች እውነትና ፍትሕ ናቸው፤+נ [ኑን] መመሪያዎቹ ሁሉ እምነት የሚጣልባቸው ናቸው።+ ס [ሳሜኽ]   አሁንም ሆነ ለዘላለም፣ ምንጊዜም አስተማማኝ* ናቸው፤ע [አይን] በእውነትና በጽድቅ ላይ የተመሠረቱ ናቸው።+ פ []   ሕዝቡን ዋጀ።+ צ [ጻዴ] ቃል ኪዳኑ ለዘላለም እንዲጸና አዘዘ። ק [ኮፍ] ስሙ ቅዱስና እጅግ የሚፈራ ነው።+ ר [ረሽ] 10  ይሖዋን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው።+ ש [ሺን] መመሪያዎቹን የሚጠብቁ* ሁሉ ጥሩ ማስተዋል አላቸው።+ ת [ታው] ውዳሴው ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ወይም “ቸርና።”
ወይም “ጽኑ መሠረት ያላቸው።”
ቃል በቃል “እነሱን የሚጠብቁ።”