የይሖዋ ምሥክሮች ባዘጋጁት የሦስት ቀን የክልል ስብሰባ ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ጋብዘንዎታል።

የስብሰባው ጉልህ ገጽታዎች

  • ንግግሮችና ቃለ መጠይቆች፦ በአሁኑ ጊዜም ሆነ ወደፊት የሚያጋጥሙንን ተፈታታኝ ሁኔታዎች በድፍረት መቋቋም የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይብራራል።

  • በቪዲዮና በድምፅ ብቻ የሚቀርቡ ፕሮግራሞች፦ እንደ እኛው ካሉ ሰዎች ሌላው ቀርቶ ከእንስሳትም እንኳ ስለ ድፍረት ምን ትምህርት እንደምናገኝ እንመለከታለን።

  • የሕዝብ ንግግር፦ ኢየሱስ፣ ልጁን በሞት ላጣ አንድ አባት “አትፍራ” ያለው ለምን እንደሆነ ይብራራል። (ማርቆስ 5:36) “የትንሣኤ ተስፋ ደፋር እንድንሆን የሚረዳን እንዴት ነው?” በሚል ርዕስ እሁድ ጠዋት የሚቀርበውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሕዝብ ንግግር እንዲያዳምጡ እንጋብዝዎታለን።

  • ፊልም፦ እሁድ ከሰዓት በኋላ በሚቀርበው ፊልም ላይ ዮናስ የተሰጠውን ተልእኮ የፈራውና የሸሸው ለምን እንደሆነ ይታያል።

እነማን መገኘት ይችላሉ?

መገኘት የሚፈልግ ሰው ሁሉ። መግቢያ በነፃ ነው፤ ሙዳየ ምጽዋትም አይዞርም።

ሙሉውን የስብሰባ ፕሮግራም እና ትላልቅ ስብሰባዎቻችን ምን እንደሚመስሉ የሚያሳይ ቪዲዮ እንዲመለከቱ እንጋብዝዎታለን።