መዝሙር 8:1-9

  • የአምላክ ክብርና የሰው ክብር

    • ‘ስምህ ምንኛ የከበረ ነው!’ (1,9)

    • “ሟች ሰው ምንድን ነው?” (4)

    • ‘የግርማ ዘውድ ደፋህለት’ (5)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በጊቲት።* የዳዊት ማህሌት። 8  ጌታችን ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ በመላው ምድር ላይ ምንኛ የከበረ ነው፤ግርማህ ከሰማያትም በላይ ከፍ ከፍ እንዲል አድርገሃል!*+  2  ከባላጋራዎችህ የተነሳ፣ከልጆችና ከሕፃናት አፍ በሚወጡ ቃላት+ ብርታትህን አሳየህ፤ይህም ጠላትንና ተበቃይን ዝም ለማሰኘት ነው።  3  የጣቶችህን ሥራ ሰማያትን፣አንተ የሠራሃቸውን ጨረቃንና ከዋክብትን ስመለከት፣+  4  ታስበው ዘንድ ሟች ሰው ምንድን ነው?ትንከባከበውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?+  5  ከመላእክት* በጥቂቱ አሳነስከው፤የክብርና የግርማ ዘውድም ደፋህለት።  6  በእጆችህ ሥራዎች ላይ ሥልጣን ሰጠኸው፤+ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አደረግክለት፦  7  መንጎቹንና ከብቶቹን ሁሉ፣እንዲሁም የዱር አራዊትን፣+  8  የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሣዎችን፣በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትን ሁሉ ከእግሩ በታች አደረግክለት።  9  ጌታችን ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ በመላው ምድር ላይ ምንኛ የከበረ ነው!

የግርጌ ማስታወሻዎች

“ግርማህ ከሰማያት በላይ የተነገረ!” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “እንደ አምላክ ካሉት።”