መዝሙር 91:1-16

  • በአምላክ ሚስጥራዊ ቦታ ጥበቃ ማግኘት

    • ከወፍ አዳኙ ወጥመድ መዳን (3)

    • በአምላክ ክንፎች ሥር መጠጊያ ማግኘት (4)

    • ‘በአጠገብህ ሺህ ቢወድቁም ወደ አንተ አይደርስም’ (7)

    • “መላእክቱን ስለ አንተ ያዛል” (11)

91  በልዑል አምላክ ሚስጥራዊ ቦታ የሚኖር ሰው+ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ጥላ ሥር ይቀመጣል።+   ይሖዋን “አንተ መጠጊያዬና ምሽጌ፣+የምታመንብህም አምላኬ ነህ”+ እለዋለሁ።   እሱ ከወፍ አዳኙ ወጥመድ፣ከአውዳሚ ቸነፈርም ይታደግሃልና።   በላባዎቹ ይከልልሃል፤*በክንፎቹም ሥር መጠጊያ ታገኛለህ።+ ታማኝነቱ+ ትልቅ ጋሻና+ መከላከያ ቅጥር* ይሆንልሃል።   በሌሊት የሚያሸብሩ ነገሮችን፣በቀንም የሚወነጨፍ ፍላጻን አትፈራም፤+   በጨለማ የሚያደባ ቸነፈርም ሆነበቀትር የሚረፈርፍ ጥፋት አያስፈራህም።   በአጠገብህ ሺህ፣በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ወደ አንተ ግን አይደርስም።+   በክፉዎች ላይ የሚደርሰውን ቅጣት* ትመለከታለህ፤በዓይንህ ብቻ ታየዋለህ።   ምክንያቱም “ይሖዋ መጠጊያዬ ነው” ብለሃል፤ ልዑሉን አምላክ መኖሪያህ* አድርገኸዋል፤+ 10  ምንም ዓይነት አደጋ አይደርስብህም፤+አንዳችም መቅሰፍት ወደ ድንኳንህ አይጠጋም። 11  በመንገድህ ሁሉ እንዲጠብቁህ+መላእክቱን ስለ አንተ ያዛልና።+ 12  እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው+በእጃቸው ያነሱሃል።+ 13  የአንበሳውን ግልገልና ጉበናውን* ትረግጣለህ፤ደቦል አንበሳውንና ትልቁን እባብ ከእግርህ ሥር ትጨፈልቃለህ።+ 14  አምላክ እንዲህ ብሏል፦ “ስለወደደኝ፣* እታደገዋለሁ።+ ስሜን ስለሚያውቅ* እጠብቀዋለሁ።+ 15  ይጠራኛል፤ እኔም እመልስለታለሁ።+ በተጨነቀ ጊዜ ከእሱ ጋር እሆናለሁ።+ እታደገዋለሁ እንዲሁም አከብረዋለሁ። 16  ረጅም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤+የማዳን ሥራዎቼንም እንዲያይ* አደርገዋለሁ።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ማንም አጠገብህ እንዳይደርስ በላባዎቹ ይከልልሃል።”
ወይም “ምሽግ።”
ቃል በቃል “በቀል።”
“ምሽግህ፤ መጠጊያህ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
በእስያና በአፍሪካ የሚገኝ እጅግ መርዘኛ የሆነ እባብ፤ ኮብራ።
ቃል በቃል “ከእኔ ጋር ስለተቆራኘ።”
ወይም “ለስሜ እውቅና ስለሚሰጥ።”
ወይም “የእኔን ማዳን እንዲያይ።”