መዝሙር 121:1-8

  • ይሖዋ ሕዝቡን ይጠብቃል

    • ‘እርዳታ የማገኘው ከይሖዋ ነው’ (2)

    • ይሖዋ ፈጽሞ አያንቀላፋም (3, 4)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። 121  ዓይኖቼን ወደ ተራሮች አነሳለሁ።+ እርዳታ የማገኘው ከየት ነው?   እኔን የሚረዳኝሰማይንና ምድርን የሠራው ይሖዋ ነው።+   እሱ እግርህ እንዲንሸራተት* ፈጽሞ አይፈቅድም።+ ጠባቂህ በጭራሽ አያንቀላፋም።   እነሆ፣ እስራኤልን የሚጠብቀው፣ፈጽሞ አያንቀላፋም፤ ደግሞም አይተኛም።+   ይሖዋ ይጠብቅሃል። ይሖዋ በቀኝህ ሆኖ+ ይጋርድሃል።+   ቀን ፀሐይ አይመታህም፤+ሌሊትም ጨረቃ አይጎዳህም።+   ይሖዋ ከማንኛውም ጉዳት ይጠብቅሃል።+ እሱ ሕይወትህን* ይጠብቃል።+   ይሖዋ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣በምታደርገው ነገር ሁሉ ይጠብቅሃል።*

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “እሱ እግርህ እንዲውተረተር።”
ወይም “ነፍስህን።”
ቃል በቃል “መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።”