መዝሙር 9:1-20

  • የአምላክን ድንቅ ሥራዎች ማወጅ

    • ይሖዋ አስተማማኝ መጠጊያ ነው (9)

    • “ስምህን የሚያውቁ በአንተ ይታመናሉ” (10)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በሙትላቤን።* የዳዊት ማህሌት። א [አሌፍ] 9  ይሖዋ ሆይ፣ በሙሉ ልቤ አወድስሃለሁ፤ስለ ድንቅ ሥራዎችህ ሁሉ እናገራለሁ።+   በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤ልዑል አምላክ ሆይ፣ ለስምህ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+ ב [ቤት]   ጠላቶቼ ወደ ኋላ ሲያፈገፍጉ+ተሰናክለው ከፊትህ ይጠፋሉ።   ለማቀርበው ትክክለኛ ክስ ትሟገትልኛለህና፤በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ በጽድቅ ትፈርዳለህ።+ ג [ጊሜል]   ብሔራትን ገሠጽክ፤+ ክፉውንም አጠፋህ፤ስማቸውን ለዘላለም ደመሰስክ።   ጠላቶች ለዘላለም ጠፍተዋል፤ከተሞቻቸውን አፈራርሰሃል፤መታሰቢያቸውም ሁሉ ይደመሰሳል።+ ה []   ይሖዋ ግን በዙፋኑ ላይ ለዘላለም ተቀምጧል፤+ዙፋኑንም ለፍትሕ ሲል አጽንቷል።+   ዓለምን* በጽድቅ ይዳኛል፤+ለብሔራት ትክክለኛ የፍርድ ውሳኔዎች ያስተላልፋል።+ ו [ዋው]   ይሖዋ ለተጨቆኑ አስተማማኝ መጠጊያ ይሆናል፤+በመከራ ጊዜ አስተማማኝ መጠጊያ ነው።+ 10  ስምህን የሚያውቁ በአንተ ይታመናሉ፤+ይሖዋ ሆይ፣ አንተን የሚሹትን ፈጽሞ አትተዋቸውም።+ ז [ዛየን] 11  በጽዮን ለሚኖረው ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ሥራውንም በሕዝቦች መካከል አስታውቁ።+ 12  ደማቸውን የሚበቀለው እሱ ያስታውሳቸዋልና፤+የተጎሳቆሉ ሰዎች የሚያሰሙትን ጩኸት አይረሳም።+ ח [ኼት] 13  ይሖዋ ሆይ፣ ቸርነት አሳየኝ፤ከሞት ደጆች የምታነሳኝ አምላክ ሆይ፣+ የሚጠሉኝ ሰዎች የሚያደርሱብኝን እንግልት ተመልከት፤ 14  ያን ጊዜ የሚያስመሰግኑ ተግባሮችህን በጽዮን ሴት ልጅ ደጆች አውጃለሁ፤+በማዳን ሥራህም ሐሴት አደርጋለሁ።+ ט [ቴት] 15  ብሔራት፣ ራሳቸው በቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ገቡ፤የገዛ እግራቸው በስውር ባስቀመጡት መረብ ተያዘ።+ 16  ይሖዋ በሚወስደው የፍርድ እርምጃ ይታወቃል።+ ክፉ ሰው በገዛ እጁ በሠራው ነገር ተጠመደ።+ ሂጋዮን።* (ሴላ) י [ዮድ] 17  ክፉ ሰው፣ አምላክን የሚረሱ ብሔራትም ሁሉወደ መቃብር* ይሄዳሉ። 18  ድሃ ግን ለዘላለም ተረስቶ አይቀርም፤+የየዋሆችም ተስፋ ፈጽሞ ከንቱ ሆኖ አይቀርም።+ כ [ካፍ] 19  ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ! ሟች የሆነ ሰው እንዲያይል አትፍቀድ። ብሔራት በፊትህ ይፈረድባቸው።+ 20  ይሖዋ ሆይ፣ ፍርሃት ልቀቅባቸው፤+ሕዝቦች ሟች መሆናቸውን ይወቁ። (ሴላ)

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ፍሬያማ የሆነችውን ምድር።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።