መዝሙር 45:1-17

  • የተቀባው ንጉሥ ጋብቻ

    • ጸጋ የተላበሱ ቃላት (2)

    • “አምላክ ለዘላለም ዙፋንህ ነው” (6)

    • ንጉሡ በሙሽራዋ ውበት ተማርኳል (11)

    • ወንዶች ልጆች በምድር ሁሉ ላይ መኳንንት ይሆናሉ (16)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በአበቦች” የሚዘመር። የቆሬ ልጆች።+ ማስኪል።* የፍቅር መዝሙር። 45  መልካም የሆነ ነገር ልቤን አነሳስቶታል። “መዝሙሬ* ስለ አንድ ንጉሥ ነው”+ እላለሁ። አንደበቴ የተዋጣለት ገልባጭ *+ እንደሚጠቀምበት ብዕር+ ይሁን።   አንተ ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ። ከከንፈሮችህ ጸጋ የተላበሱ ቃላት ይፈስሳሉ።+ አምላክ ለዘላለም የባረከህ ለዚህ ነው።+   ኃያል ሆይ፣+ ሰይፍህን+ በጎንህ ታጠቅ፤ክብርህንና ግርማህንም+ ተጎናጸፍ።   በግርማህም ድል ለመቀዳጀት* ገስግስ፤+ፈረስህን እየጋለብክ ለእውነት፣ ለትሕትናና ለጽድቅ ተዋጋ፤+ቀኝ እጅህም የሚያስፈሩ ተግባሮችን ያከናውናል።*   ፍላጻዎችህ የሾሉ ናቸው፤ ሰዎችን በፊትህ ይረፈርፋሉ፤+የንጉሡን ጠላቶች ልብ ይወጋሉ።+   አምላክ ለዘላለም ዙፋንህ ነው፤+የመንግሥትህ በትር የቅንነት* በትረ መንግሥት ነው።+   ጽድቅን ወደድክ፤+ ክፋትን ጠላህ።+ ስለዚህ አምላክ ይኸውም አምላክህ ከባልንጀሮችህ ይበልጥ በደስታ ዘይት+ ቀባህ።+   ልብሶችህ ሁሉ የከርቤ፣ የእሬትና* የብርጉድ መዓዛ አላቸው፤በዝሆን ጥርስ ካጌጠው ታላቅ ቤተ መንግሥት የሚወጣው የባለ አውታር መሣሪያዎች* ድምፅ ያስደስትሃል።   ከተከበሩት እመቤቶችህ መካከል የነገሥታት ልጆች ይገኛሉ። እቴጌይቱ* በኦፊር ወርቅ+ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች። 10  ልጄ ሆይ፣ አዳምጪ፣ ልብ በዪ፣ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ። 11  ንጉሡም በውበትሽ ተማርኳል፤እሱ ጌታሽ ነውና፣እጅ ንሺው። 12  የጢሮስ ሴት ልጅ ስጦታ ይዛ ትመጣለች፤እጅግ ባለጸጋ የሆኑትም በአንቺ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ጥረት ያደርጋሉ። 13  የንጉሡ ሴት ልጅ እጅግ ተውባ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ተቀምጣለች፤*ልብሷ በወርቅ ያጌጠ* ነው። 14  ያጌጠ ልብሷን* ለብሳ ወደ ንጉሡ ትወሰዳለች። ወዳጆቿ የሆኑ ደናግል አጃቢዎቿን ወደ ፊትህ ያቀርቧቸዋል። 15  በደስታና በሐሴት ይመሯቸዋል፤ወደ ንጉሡ ቤተ መንግሥት ይገባሉ። 16  በአባቶችህ ፋንታ ወንዶች ልጆችህ ይተካሉ። በምድር ሁሉ ላይ መኳንንት አድርገህ ትሾማቸዋለህ።+ 17  ለሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ስምህን አሳውቃለሁ።+ በመሆኑም ሕዝቦች ለዘላለም ያወድሱሃል።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ሥራዎቼ።”
ወይም “ጸሐፊ።”
ወይም “ስኬት ለማግኘት።”
ቃል በቃል “ያስተምርሃል።”
ወይም “የፍትሕ።”
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሽቶ ለመሥራት የሚያገለግል ጥሩ መዓዛ ያለው ንጥረ ነገር የሚገኝበትን ዛፍ ያመለክታል።
ወይም “የሙዚቃ መሣሪያዎች።”
ወይም “ንግሥቲቱ።”
ቃል በቃል “ተውባ ውስጥ ተቀምጣለች።”
ቃል በቃል “ወርቀ ዘቦ።”
“በጥልፍ ሥራ የተዋበ ቀሚሷን” ማለትም ሊሆን ይችላል።