መዝሙር 75:1-10

  • አምላክ በትክክል ይፈርዳል

    • ክፉዎች የይሖዋን ጽዋ ይጠጣሉ (8)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። “ጥፋት አታምጣ” በተባለው ቅኝት የሚዜም ማህሌት። የአሳፍ+ መዝሙር። 75  ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ አምላክ ሆይ፣ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ስምህ ከእኛ ጋር ነው፤+ሰዎችም ድንቅ ሥራዎችህን ያውጃሉ።  2  አንተ እንዲህ ትላለህ፦ “ጊዜ ስወስንበትክክል እፈርዳለሁ።  3  ምድርና በላይዋ የሚኖሩ ሁሉ ሲቀልጡ፣ምሰሶዎቿን አጽንቼ ያቆምኩት እኔ ነኝ።” (ሴላ)  4  ጉራቸውን ለሚነዙት “ጉራ አትንዙ” እላለሁ፤ ክፉዎቹንም እንዲህ እላለሁ፦ “ኃይላችሁን* ከፍ ከፍ አታድርጉ።  5  ኃይላችሁን* ወደ ላይ ከፍ አታድርጉ፤ወይም በትዕቢት አትናገሩ።  6  ክብር ከምሥራቅም ሆነ ከምዕራብወይም ከደቡብ አይመጣምና።  7  አምላክ ፈራጅ ነውና።+ አንዱን ያዋርዳል፤ ሌላውን ደግሞ ከፍ ከፍ ያደርጋል።+  8  በይሖዋ እጅ ጽዋ አለና፤+የወይን ጠጁ አረፋ ያወጣል፤ ደግሞም ሙሉ በሙሉ የተደባለቀ ነው። እሱ በእርግጥ ያፈሰዋል፤በምድርም ላይ ያሉ ክፉዎች ሁሉ ከነአተላው ይጨልጡታል።”+  9  እኔ ግን ይህን ለዘላለም አውጃለሁ፤ለያዕቆብ አምላክ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ። 10  እሱ እንዲህ ይላልና፦ “የክፉዎችን ኃይል* በሙሉ እቆርጣለሁ፤የጻድቅ ሰው ኃይል ግን ከፍ ከፍ ይላል።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ቀንዳችሁን።”
ቃል በቃል “ቀንዳችሁን።”
ቃል በቃል “ቀንድ።”