መዝሙር 109:1-31
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።
109 የማወድስህ አምላክ ሆይ፣+ ዝም አትበል።
2 ክፉዎችና አታላዮች በእኔ ላይ አፋቸውን ይከፍታሉና።
ስለ እኔ በሐሰተኛ አንደበት ይናገራሉ፤+
3 በዙሪያዬም ሆነው የጥላቻ ቃላት ይሰነዝሩብኛል፤ያለምክንያት ያጠቁኛል።+
4 ፍቅር ሳሳያቸው በምላሹ ይቃወሙኛል፤+እኔ ግን መጸለዬን እቀጥላለሁ።
5 ለመልካም ነገር ክፋትን፣ላሳየኋቸው ፍቅር ጥላቻን ይመልሱልኛል።+
6 በእሱ ላይ ክፉ ሰው እዘዝበት፤በቀኙም ተቃዋሚ* ይቁም።
7 ፍርድ ፊት ሲቆም በደለኛ* ሆኖ ይገኝ፤ጸሎቱም እንኳ እንደ ኃጢአት ይቆጠርበት።+
8 የሕይወት ዘመኑ አጭር ይሁን፤+የበላይ ተመልካችነት ሹመቱን ሌላ ሰው ይውሰደው።+
9 ልጆቹ* ያለአባት ይቅሩ፤ሚስቱም መበለት ትሁን።
10 ልጆቹ* በየቦታው የሚቅበዘበዙ ለማኞች ይሁኑ፤ከፈራረሰው መኖሪያቸው ወጥተው ምግብ ፍለጋ ይንከራተቱ።
11 ያበደረው ሰው ያለውን ነገር ሁሉ ይውሰድበት፤*ባዕድ ሰዎችም ንብረቱን ይዝረፉት።
12 ደግነት* የሚያሳየው ሰው ከቶ አይኑር፤ያለአባት ለቀሩት ልጆቹ የሚራራ አንድም ሰው አይገኝ።
13 ዘሩ* ይጥፋ፤+ስማቸው በአንድ ትውልድ ውስጥ ይደምሰስ።
14 አባቶቹ የሠሩትን በደል ይሖዋ አይርሳ፤+የእናቱም ኃጢአት አይደምሰስ።
15 ይሖዋ የሠሩትን ነገር ምንጊዜም ያስብ፤መታሰቢያቸውንም ከምድር ገጽ ያጥፋ።+
16 ክፉው ሰው ደግነት* ለማሳየት አላሰበምና፤+ይልቁንም የተጨቆነውን፣ ድሃውንና ልቡ በሐዘን የተደቆሰውን ሰውለመግደል ሲያሳድድ ነበር።+
17 ሌሎችን መርገም ወደደ፤ በመሆኑም እርግማኑ በእሱ ላይ ደረሰበት፤ሌሎችን ለመባረክ ፍላጎት አልነበረውም፤ ስለዚህ ምንም በረከት አላገኘም።
18 እርግማንን እንደ ልብስ ለበሰ።
እንደ ውኃም ሰውነቱ ውስጥ ፈሰሰ፤እንደ ዘይት ወደ አጥንቶቹ ዘለቀ።
19 እርግማኑ እንደሚከናነበው ልብስ፣ሁልጊዜ እንደሚታጠቀውም ቀበቶ ይሁንለት።+
20 እኔን የሚቃወመኝ ሰው፣በእኔም* ላይ ክፉ ነገር የሚናገሩ ሰዎች ከይሖዋ የሚያገኙት ዋጋ ይህ ነው።+
21 አንተ ግን ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ለስምህ ስትል እርዳኝ።+
ታማኝ ፍቅርህ ጥሩ ስለሆነ ታደገኝ።+
22 እኔ ምስኪንና ድሃ ነኝና፤+ልቤም በውስጤ ተወግቷል።+
23 ፀሐይ ስትጠልቅ እንደሚጠፋ ጥላ አልፋለሁ፤እንደ አንበጣ አራግፈው ጣሉኝ።
24 ከመጾሜ የተነሳ ጉልበቶቼ ከዱኝ፤ሰውነቴ ከሳ፤ እኔም እየመነመንኩ ሄድኩ።*
25 የእነሱ መሳለቂያ ሆንኩ።+
ሲያዩኝ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።+
26 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እርዳኝ፤በታማኝ ፍቅርህ አድነኝ።
27 ይህ የአንተ እጅ መሆኑን ይወቁ፤ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ያደረግከው አንተ እንደሆንክ ይገንዘቡ።
28 እነሱ ይራገሙ፤ አንተ ግን ባርክ።
እነሱ በእኔ ላይ ሲነሱ ለኀፍረት ይዳረጉ፤አገልጋይህ ግን ሐሴት ያድርግ።
29 እኔን የሚቃወሙኝ ውርደት ይከናነቡ፤ኀፍረታቸውንም እንደ ልብስ* ይጎናጸፉ።+
30 አንደበቴ ይሖዋን ከልብ ታወድሰዋለች፤በብዙ ሕዝቦች ፊት አወድሰዋለሁ።+
31 በእሱ* ላይ ከሚፈርዱት ሊያድነውበድሃው ቀኝ ይቆማልና።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ከሳሽ።”
^ ወይም “ክፉ።”
^ ቃል በቃል “ወንዶች ልጆቹ።”
^ ቃል በቃል “ወንዶች ልጆቹ።”
^ ወይም “አራጣ አበዳሪዎች ወጥመድ ይዘርጉበት።”
^ ወይም “ታማኝ ፍቅር።”
^ ወይም “ትውልዱ።”
^ ወይም “ታማኝ ፍቅር።”
^ ወይም “በነፍሴም።”
^ ቃል በቃል “ሥጋዬ ኮሰመነ፤ ስብም (ዘይትም) የለውም።”
^ ወይም “እጅጌ እንደሌለው ቀሚስ።”
^ ወይም “በነፍሱ።”