መዝሙር 11:1-7

  • ይሖዋን መጠጊያ ማድረግ

    • “ይሖዋ ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው” (4)

    • አምላክ ዓመፅን የሚወድን ሰው ይጠላል (5)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር። 11  ይሖዋን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ።+ ታዲያ እንዴት እንዲህ ትሉኛላችሁ?* “እንደ ወፍ ወደ ተራራህ ብረር!*   ክፉዎች ደጋናቸውን እንዴት እንደወጠሩ ተመልከት፤በጨለማ፣ ልበ ቀና የሆኑትን ለመውጋት፣ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል።   መሠረቶቹ* ከተናዱ፣ጻድቁ ሰው ምን ማድረግ ይችላል?”   ይሖዋ ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው።+ የይሖዋ ዙፋን በሰማያት ነው።+ የገዛ ዓይኖቹ ይመለከታሉ፤ ንቁ የሆኑት* ዓይኖቹ የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።+   ይሖዋ ጻድቁንም ሆነ ክፉውን ይመረምራል፤+ዓመፅን* የሚወድን ማንኛውንም ሰው ይጠላል።*+   በክፉዎች ላይ ወጥመድ* ያዘንባል፤እሳትና ድኝ+ እንዲሁም የሚለበልብ ነፋስ ጽዋቸው ይሆናል።   ይሖዋ ጻድቅ ነውና፤+ የጽድቅ ሥራዎችን ይወዳል።+ ቅን የሆኑ ሰዎች ፊቱን ያያሉ።*+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ነፍሴን እንዴት እንዲህ ትሏታላችሁ?”
ቃል በቃል “ወደ ተራራችሁ ብረሩ።”
ወይም “የፍትሕ መሠረቶች።”
ወይም “የሚያበሩት።”
ወይም “ነፍሱ ትጠላዋለች፤ ሁለንተናው ይጠላዋል።”
ጠብን፣ ድብድብንና ጉዳት ማድረስን ያመለክታል።
“ፍም” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ሞገሱን ያገኛሉ።”