መዝሙር 124:1-8

  • “ይሖዋ ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ”

    • ከተሰበረ ወጥመድ ማምለጥ (7)

    • “የይሖዋ ስም ረዳታችን ነው” (8)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። የዳዊት መዝሙር። 124  “ይሖዋ ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ፣”+ እስራኤል እንዲህ ይበል፦  2  “ይሖዋ ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ፣+ሰዎች እኛን ለማጥቃት በተነሱ ጊዜ፣+  3  ቁጣቸው በእኛ ላይ በነደደ ጊዜ፣+በሕይወት ሳለን በዋጡን ነበር።+  4  በዚያን ጊዜ ውኃ ጠራርጎ በወሰደን፣ጎርፍም ባጥለቀለቀን ነበር።*+  5  ኃይለኛ ውኃ በዋጠን ነበር።*  6  ለጥርሳቸው ሲሳይ እንድንሆን አሳልፎ ስላልሰጠንይሖዋ ይወደስ።  7  ከአዳኝ ወጥመድእንዳመለጠች ወፍ ነን፤*+ወጥመዱ ተሰበረ፤እኛም አመለጥን።+  8  ሰማይንና ምድርን የሠራውየይሖዋ ስም ረዳታችን ነው።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ነፍሳችንን ጎርፍ ባጥለቀለቃት ነበር።”
ወይም “ነፍሳችንን በዋጣት ነበር።”
ወይም “ነፍሳችን ከአዳኝ ወጥመድ እንዳመለጠች ወፍ ነች።”