መዝሙር 149:1-9

  • አምላክን ለተቀዳጀው ድል በመዝሙር ማወደስ

    • አምላክ በሕዝቡ ደስ ይሰኛል (4)

    • የአምላክ ታማኝ አገልጋዮች ክብር ይገባቸዋል (9)

149  ያህን አወድሱ!* ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤+በታማኝ አገልጋዮች ጉባኤ መካከል አወድሱት።+  2  እስራኤል በታላቅ ሠሪው+ ሐሴት ያድርግ፤የጽዮን ልጆች በንጉሣቸው ደስ ይበላቸው።  3  ስሙን በሽብሸባ ያወድሱ፤+በአታሞና በበገና የውዳሴ መዝሙር ይዘምሩለት።+  4  ይሖዋ በሕዝቡ ደስ ይሰኛልና።+ እሱ የዋሆችን በማዳን ውበት ያጎናጽፋቸዋል።+  5  ታማኝ አገልጋዮቹ በክብር ሐሴት ያድርጉ፤በመኝታቸው ላይ ሆነው እልል ይበሉ።+  6  አንደበታቸው አምላክን የሚያወድስ መዝሙር ይዘምር፤እጃቸውም በሁለቱም በኩል የተሳለ ሰይፍ ይያዝ፤  7  ይህም በብሔራት ላይ የበቀል እርምጃ እንዲወስዱ፣ሕዝቦችንም እንዲቀጡ፣  8  ነገሥታታቸውን በሰንሰለት፣በመካከላቸው ያሉትን ታላላቅ ሰዎችም በእግር ብረት እንዲያስሩ፣  9  ደግሞም በእነሱ ላይ የተላለፈውን በጽሑፍ የሰፈረ ፍርድ እንዲፈጽሙ ነው።+ ታማኝ አገልጋዮቹ ሁሉ ይህ ክብር ይገባቸዋል። ያህን አወድሱ!*

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።