በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥያቄ 6

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መሲሑ ምን ትንቢት ተናግሯል?

 ትንቢት

“ከይሁዳ አእላፋት መካከል በጣም ትንሽ የሆንሽው ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ፣ . . . በእስራኤል ገዢ የሚሆን ከአንቺ ይወጣልኛል።”

ሚክያስ 5:2

ፍጻሜ

“በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ኢየሱስ በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም ከተወለደ በኋላ ኮከብ ቆጣሪዎች ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም [መጡ]።”

ማቴዎስ 2:1

 ትንቢት

“መደረቢያዎቼን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ፤ በልብሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።”

መዝሙር 22:18

ፍጻሜ

“ወታደሮቹ ኢየሱስን በእንጨት ላይ ከቸነከሩት በኋላ መደረቢያዎቹን ወስደው . . . አራት ቦታ ቆራረጧቸው፤ ከውስጥ ለብሶት የነበረውንም ልብስ ወሰዱ። ሆኖም ልብሱ ከላይ እስከ ታች አንድ ወጥ ሆኖ ያለስፌት የተሠራ ነበር። ስለዚህ እርስ በርሳቸው ‘ከምንቀደው ዕጣ ተጣጥለን ለማን እንደሚደርስ እንወስን’ ተባባሉ።”

ዮሐንስ 19:23, 24

 ትንቢት

“አጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤ አንዳቸውም ቢሆኑ አልተሰበሩም።”

መዝሙር 34:20

ፍጻሜ

“ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን ቀደም ብሎ መሞቱን ስላዩ እግሮቹን አልሰበሩም።”

ዮሐንስ 19:33

 ትንቢት

“ስለ መተላለፋችን ተወጋ።”

ኢሳይያስ 53:5

ፍጻሜ

“ከወታደሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ፈሰሰ።”

ዮሐንስ 19:34

 ትንቢት

“እነሱም ደሞዜን፣ 30 የብር ሰቅል ከፈሉኝ።”

ዘካርያስ 11:12, 13

ፍጻሜ

“ከዚህ በኋላ፣ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ ‘እሱን አሳልፌ ብሰጣችሁ ምን ትሰጡኛላችሁ?’ አላቸው። እነሱም 30 የብር ሳንቲሞች ሊሰጡት ተስማሙ።”

ማቴዎስ 26:14, 1527:5