መዝሙር 63:1-11

  • አምላክን መናፈቅ

    • ‘ታማኝ ፍቅርህ ከሕይወት ይሻላል’ (3)

    • ‘ምርጥ የሆነውን በልቼ ጠገብኩ’ (5)

    • ሌሊት ስለ አምላክ ማሰላሰል (6)

    • ‘አምላክን የሙጥኝ እላለሁ’ (8)

የዳዊት ማህሌት፤ በይሁዳ ምድረ በዳ በነበረበት ጊዜ።+ 63  አምላክ ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ዘወትር እጠባበቃለሁ።+ አንተን ተጠማሁ።*+ ውኃ በሌለበት ደረቅና የተጠማ ምድርአንተን ከመናፈቄ የተነሳ እጅግ ዝያለሁ።*+   ስለዚህ በቅዱሱ ስፍራ አንተን ተመለከትኩ፤ብርታትህንና ክብርህን አየሁ።+   ታማኝ ፍቅርህ ከሕይወት ስለሚሻል+የገዛ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።+   በመሆኑም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አወድስሃለሁ፤በአንተም ስም እጆቼን ወደ ላይ አነሳለሁ።   ምርጥ የሆነውንና ስቡን በልቼ ጠገብኩ፤*ስለዚህ በከንፈሬ እልልታ አፌ ያወድስሃል።+   መኝታዬ ላይ ሆኜ አንተን አስታውሳለሁ፤ሌሊት* ስለ አንተ አሰላስላለሁ።+   አንተ ረዳቴ ነህና፤+በክንፎችህም ጥላ ሥር ሆኜ እልል እላለሁ።+   አንተን የሙጥኝ እላለሁ፤*ቀኝ እጅህ አጥብቆ ይይዘኛል።+   ሕይወቴን ለማጥፋት* የሚሹ ሰዎች ግንወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ። 10  ለሰይፍ ስለት አልፈው ይሰጣሉ፤የቀበሮዎችም ምግብ ይሆናሉ። 11  ንጉሡ ግን በአምላክ ሐሴት ያደርጋል። በእሱ የሚምል ሰው ሁሉ ይደሰታል፤*ሐሰትን የሚናገሩ ሰዎች አፍ ይዘጋልና።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ነፍሴ አንተን ተጠማች።”
ቃል በቃል “ሥጋዬ አንተን ከመናፈቋ የተነሳ እጅግ ዝላለች።”
ወይም “ነፍሴ ምርጥ የሆነውንና ስቡን በልታ ጠገበች።”
ወይም “በክፍለ ሌሊቶች።”
ወይም “ነፍሴ አንተን የሙጥኝ ትላለች።”
ወይም “ነፍሴን ለማጥፋት፤ እኔን ለመግደል።”
ወይም “ይኮራል።”