መዝሙር 56:1-13

  • ስደት በደረሰበት ጊዜ ያቀረበው ጸሎት

    • “በአምላክ እታመናለሁ” (4)

    • “እንባዬን በአቁማዳህ አጠራቅም” (8)

    • “ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” (4, 11)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “ራቅ ባለ ቦታ የምትገኝ ዝምተኛ ርግብ” በተባለው ቅኝት። የዳዊት መዝሙር። ሚክታም።* ፍልስጤማውያን በጌት በያዙት ጊዜ።+ 56  አምላክ ሆይ፣ ሟች የሆነ ሰው ጥቃት እየሰነዘረብኝ* ስለሆነ ሞገስ አሳየኝ። ቀኑን ሙሉ ይዋጉኛል፤ ደግሞም ያስጨንቁኛል።   ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ እኔን ለመንከስ ይሞክራሉ፤ብዙዎች በእብሪት ተነሳስተው ይዋጉኛል።   ፍርሃት በሚሰማኝ ጊዜ+ በአንተ እታመናለሁ።+   ቃሉን በማወድሰው አምላክ፣አዎ፣ በአምላክ እታመናለሁ፤ አልፈራም። ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?+   ቀኑን ሙሉ የእኔን ጉዳይ ለማበላሸት ይጥራሉ፤ሐሳባቸው እኔን መጉዳት ብቻ ነው።+   እኔን ለማጥቃት ራሳቸውን ይሰውራሉ፤ሕይወቴን* ለማጥፋት በመሻት+እርምጃዬን አንድ በአንድ ይከታተላሉ።+   ከክፋታቸው የተነሳ አስወግዳቸው። አምላክ ሆይ፣ ብሔራትን በቁጣህ አጥፋቸው።+   ከቦታ ቦታ ስንከራተት አንድ በአንድ ትከታተላለህ።+ እንባዬን በአቁማዳህ አጠራቅም።+ ደግሞስ በመጽሐፍህ ውስጥ ሰፍሮ የለም?+   እርዳታ ለማግኘት በምጣራበት ቀን ጠላቶቼ ያፈገፍጋሉ።+ አምላክ ከጎኔ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ።+ 10  ቃሉን በማወድሰው አምላክ፣ቃሉን በማወድሰው በይሖዋ፣ 11  አዎ፣ በአምላክ እታመናለሁ፤ አልፈራም።+ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?+ 12  አምላክ ሆይ፣ ለአንተ በተሳልኳቸው ስእለቶች የተነሳ ግዴታ ውስጥ ገብቻለሁ፤+ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ።+ 13  አንተ ከሞት ታድገኸኛልና፤*+እግሮቼንም ከእንቅፋት አድነሃል፤+ይህም በሕያዋን ብርሃን በአምላክ ፊት እመላለስ ዘንድ ነው።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “እኔን ለመንከስ እየሞከረ።”
ወይም “ነፍሴን።”
ወይም “ነፍሴን ከሞት ታድገሃታልና።”