መዝሙር 110:1-7

  • እንደ መልከጼዴቅ ያለ ንጉሥና ካህን

    • ‘በጠላቶችህ መካከል ግዛ’ (2)

    • እንደ ጤዛ ያሉ ራሳቸውን በፈቃደኝነት የሚያቀርቡ ወጣቶች (3)

የዳዊት መዝሙር። ማህሌት። 110  ይሖዋ ጌታዬን “ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ+በቀኜ ተቀመጥ”+ አለው።   ይሖዋ የኃይልህን በትር ከጽዮን ይዘረጋል፤ “በጠላቶችህ መካከል በድል አድራጊነት ግዛ”*+ ይላል።   ወደ ጦርነት በምትዘምትበት ቀን* ሕዝብህ በገዛ ፈቃዱ ራሱን ያቀርባል።በቅድስና ተውበህ ሳለ፣ ከንጋት ማህፀን እንደወጣ ጤዛ ያለ የወጣቶች ሠራዊት ከጎንህ ይሰለፋል።   ይሖዋ “እንደ መልከጼዴቅ፣+ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ!” ሲል ምሏል፤+ደግሞም ሐሳቡን አይለውጥም።*   ይሖዋ በቀኝህ ይሆናል፤+በቁጣው ቀን ነገሥታትን ያደቃል።+   በብሔራት ላይ* የፍርድ እርምጃ ይወስዳል፤+ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋል።+ ሰፊ የሆነውን አገር* የሚገዛውን መሪ* ያደቀዋል።   እሱ* በመንገድ ዳር ካለው ጅረት ይጠጣል። በመሆኑም ራሱን ቀና ያደርጋል።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “መግዛት ጀምር።”
ወይም “ሠራዊትህ ለጦርነት በሚንቀሳቀስበት ቀን።”
ወይም “አይጸጸትም።”
ወይም “መካከል።”
ወይም “መላውን ምድር።”
ቃል በቃል “ራስ።”
መዝ 110:1 ላይ “ጌታዬ” ተብሎ የተጠቀሰውን ያመለክታል።