በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥያቄ 19

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት መጻሕፍት ምን ይዘዋል?

 የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት (“ብሉይ ኪዳን”)

 ፔንታቱክ (5 መጻሕፍት)፦

ዘፍጥረት፣ ዘፀአት፣ ዘሌዋውያን፣ ዘኁልቁ፣ ዘዳግም

የፍጥረት ሥራ ከተከናወነበት ጊዜ አንስቶ የእስራኤል ብሔር እስከተቋቋመበት ጊዜ ድረስ

 ታሪካዊ ዘገባዎችን የያዙ መጻሕፍት (12 መጻሕፍት)፦

ኢያሱ፣ መሳፍንት፣ ሩት

እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር መግባታቸውና ከዚያ በኋላ የተፈጸሙ ክንውኖች

1 ሳሙኤል፣ 2 ሳሙኤል፣ 1 ነገሥት፣ 2 ነገሥት፣ 1 ዜና መዋዕል፣ 2 ዜና መዋዕል

ኢየሩሳሌም እስከጠፋችበት ጊዜ ድረስ ያለው የእስራኤል ብሔር ታሪክ

ዕዝራ፣ ነህምያ፣ አስቴር

ከባቢሎን ግዞት ከተመለሱ በኋላ ያለው የአይሁዳውያን ታሪክ

 የቅኔ ይዘት ያላቸው መጻሕፍት (5 መጻሕፍት)፦

ኢዮብ፣ መዝሙር፣ ምሳሌ፣ መክብብ፣ መኃልየ መኃልይ

ጥበብ ያዘሉ ምሳሌዎችና መዝሙሮች

 የትንቢት መጻሕፍት (17 መጻሕፍት)፦

ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ሰቆቃወ ኤርምያስ፣ ሕዝቅኤል፣ ዳንኤል፣ ሆሴዕ፣ ኢዩኤል፣ አሞጽ፣ አብድዩ፣ ዮናስ፣ ሚክያስ፣ ናሆም፣ ዕንባቆም፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣ ዘካርያስ፣ ሚልክያስ

የአምላክን ሕዝብ በተመለከተ የተነገሩ ትንቢቶች

 የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት (“አዲስ ኪዳን”)

 አራቱ ወንጌሎች (4 መጻሕፍት)፦

ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ ዮሐንስ

ስለ ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት የሚገልጽ ታሪክ

 የሐዋርያት ሥራ (1 መጽሐፍ)፦

የክርስቲያን ጉባኤ አመሠራረትና ሚስዮናውያን ያከናወኑት ሥራ

 ደብዳቤዎች (21 መጻሕፍት)፦

ሮም፣ 1 ቆሮንቶስ፣ 2 ቆሮንቶስ፣ ገላትያ፣ ኤፌሶን፣ ፊልጵስዩስ፣ ቆላስይስ፣ 1 ተሰሎንቄ፣ 2 ተሰሎንቄ

ለተለያዩ ክርስቲያን ጉባኤዎች የተላኩ ደብዳቤዎች

1 ጢሞቴዎስ፣ 2 ጢሞቴዎስ፣ ቲቶ፣ ፊልሞና

በግለሰብ ደረጃ ለክርስቲያኖች የተጻፉ ደብዳቤዎች

 ዕብራውያን፣ ያዕቆብ፣ 1 ጴጥሮስ፣ 2 ጴጥሮስ፣ 1 ዮሐንስ፣ 2 ዮሐንስ፣ 3 ዮሐንስ፣ ይሁዳ

ለክርስቲያኖች በሙሉ የተጻፉ ደብዳቤዎች

 ራእይ (1 መጽሐፍ)፦

ሐዋርያው ዮሐንስ ያያቸው የተለያዩ ራእዮች