ጥያቄ 11
ሰው ሲሞት ምን ይሆናል?
“መንፈሱ ትወጣለች፤ ወደ መሬት ይመለሳል፤ በዚያው ቀን ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል።”
“ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁም፤ . . . እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኃይልህ አከናውን፤ አንተ በምትሄድበት በመቃብር ሥራም ሆነ ዕቅድ፣ እውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና።”
“[ኢየሱስ] ‘ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቷል፤ እኔም ልቀሰቅሰው ወደዚያ እሄዳለሁ’ አላቸው። ይሁንና ኢየሱስ የተናገረው ስለመሞቱ ነበር። እነሱ ግን ለማረፍ ብሎ እንቅልፍ ስለመተኛቱ የተናገረ መሰላቸው። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ በግልጽ እንዲህ አላቸው፦ ‘አልዓዛር ሞቷል።’”