በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

አንድ የይሖዋ ምሥክር እንዲያነጋግርህ ትፈልጋለህ?

መጽሐፍ ቅዱስን መማር ወይም ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ማወቅ ትፈልጋለህ? ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ በመሙላት አንድ የይሖዋ ምሥክር እንዲያነጋግርህ ጥያቄ ማቅረብ ትችላለህ፤ ከዚያም በአካባቢህ የሚኖር አንድ የይሖዋ ምሥክር ያነጋግርሃል።

ቅጹ ላይ የሞላኸውን የግል መረጃ የምንጠቀምበት፣ አንድ የይሖዋ ምሥክር እንዲያነጋግርህ ያቀረብከውን ጥያቄ ለማስተናገድ ብቻ ነው። ይህም ከግል መረጃ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ከምንከተለው ዓለም አቀፍ ፖሊሲ ጋር የሚስማማ ነው።

በአድራሻህ ተጠቅመን እናነጋግርሃለን

ቅጹን ከሞላህ በኋላ በሳምንት ወይም በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ አንድ የይሖዋ ምሥክር ደውሎ ወይም መጥቶ ያነጋግርሃል።

ከመጽሐፍ ቅዱስ ትማራለህ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ምን እንደሚል ትማራለህ፤ በነፃ ስለምንሰጠው አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርስ መረጃ መጠየቅም ትችላለህ።

ምቹ ነው

ከአስተማሪህ ጋር፣ ከፈለግህ በአካል ካልሆነም በስልክ ወይም በቪዲዮ መገናኘት ትችላላችሁ፤ በፈለግከው ሰዓት፣ በፈለግከው ቦታ።

ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ጋር በተያያዘ የተሰጠ ማሳሰቢያ፦ በብዙ አገሮች በአካል ተገናኝቶ ሰዎችን ማወያየት ለጊዜው አቁመናል። ይህን ቅጽ ስትሞላ እባክህ ስልክህን ማካተትህን አትዘንጋ፤ ከዚያም በአቅራቢያህ የሚኖር አንድ የይሖዋ ምሥክር ያነጋግርሃል።