ጥያቄ 18

ወደ አምላክ መቅረብ የምትችለው እንዴት ነው?

 “ጸሎት ሰሚ የሆንከው አምላክ ሆይ፣ ሁሉም ዓይነት ሰው ወደ አንተ ይመጣል።”

መዝሙር 65:2

 “በሙሉ ልብህ በይሖዋ ታመን፤ ደግሞም በገዛ ራስህ ማስተዋል አትመካ። በመንገድህ ሁሉ እሱን ግምት ውስጥ አስገባ፤ እሱም ጎዳናህን ቀና ያደርገዋል።”

ምሳሌ 3:5, 6

 “የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንዲችሉ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ የሆንከውን አንተንና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ አለባቸው።”

ዮሐንስ 17:3

 “[አምላክ] ከእያንዳንዳችን የራቀ . . . አይደለም።”

የሐዋርያት ሥራ 17:27

 “ፍቅራችሁ ከአምላክ ፈቃድ ትክክለኛ እውቀትና ጥልቅ ግንዛቤ ጋር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንዲሄድ መጸለዬን እቀጥላለሁ።”

ፊልጵስዩስ 1:9

 “ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ሰው ካለ አምላክን ያለማሰለስ ይለምን፤ አምላክ ማንንም ሳይነቅፍ ለሁሉም በልግስና ይሰጣልና፤ ይህም ሰው ይሰጠዋል።”

ያዕቆብ 1:5

 “ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች እጆቻችሁን አንጹ፤ እናንተ ወላዋዮች ልባችሁን አጥሩ።”

ያዕቆብ 4:8

 “አምላክን መውደድ ማለት ትእዛዛቱን መጠበቅ ማለት ነውና፤ ትእዛዛቱ ደግሞ ከባድ አይደሉም።”

1 ዮሐንስ 5:3