ከባድ ችግሮች ሲያጋጥሙን ደስታና ውስጣዊ ሰላም የሕልም እንጀራ ሊሆንብን ይችላል። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ በርካታ ሰዎች በየዕለቱ የሚገጥማቸውን ውጥረት እንዲቋቋሙ፣ አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ችግሮችን እንዲወጡ እንዲሁም ዓላማና ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲመሩ ረድቷቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ አንተም ደስተኛ እንድትሆን ሊረዳህ ይችላል።