ጥያቄ 3
መጽሐፍ ቅዱስን የጻፈው ማን ነው?
“ሙሴ የይሖዋን ቃል ሁሉ በጽሑፍ አሰፈረ።”
“ዳንኤል በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ ሕልምና ራእዮች አየ። ከዚያም ያየውን ሕልም ጻፈ፤ ጉዳዩንም በዝርዝር አሰፈረ።”
“የአምላክን ቃል ከእኛ በሰማችሁ ጊዜ እንደ ሰው ቃል ሳይሆን እንደ አምላክ ቃል አድርጋችሁ ተቀብላችሁታል፤ ደግሞም የአምላክ ቃል ነው።”
“ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው፤ እንዲሁም ለማስተማር . . . ይጠቅማሉ።”
“መቼም ቢሆን ትንቢት በሰው ፈቃድ አልመጣምና፤ ከዚህ ይልቅ ሰዎች ከአምላክ የተቀበሉትን ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ ተገፋፍተው ተናገሩ።”