በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች ሳምንታዊ ስብሰባዎች

ሳምንታዊ ስብሰባዎቻችን ምን እንደሚመስሉ ማወቅ ትፈልጋለህ? ለአንተ ቅርብ የሆነ የመሰብሰቢያ ቦታ መፈለግ ትችላለህ።

ለአንተ ቅርብ የሆነውን ቦታ ፈልግ (አዲስ ዊንዶው ክፈት)

ሳምንታዊ ስብሰባዎቻችን ምን ይመስላሉ?

የይሖዋ ምሥክሮች በሳምንት ሁለት ቀን ለአምልኮ ይሰበሰባሉ። (ዕብራውያን 10:24, 25) ስብሰባዎቻችን ለሁሉም ሰው ክፍት ሲሆኑ በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ መጽሐፍ ቅዱስን እንመረምራለን፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኘውን ትምህርት እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደምንችል እንማራለን።

አብዛኞቹ ትምህርቶች አድማጮችን የሚያሳትፉ ሲሆን የሚቀርቡበት መንገድ በትምህርት ቤት ውስጥ ከሚደረግ ውይይት ጋር ይመሳሰላል። ተሳትፎው በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ነው። ስብሰባዎቹ የሚከፈቱትና የሚዘጉት በመዝሙርና በጸሎት ነው።

በስብሰባዎቻችን ላይ ለመገኘት የይሖዋ ምሥክር መሆን አያስፈልግህም። ማንኛውም ሰው አብሮን እንዲሰበሰብ እንጋብዛለን። ክፍያ አይጠየቅም፤ ሙዳየ ምጽዋትም አይዞርም።