የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ

ሐሙስ፣ መጋቢት 24, 2018 ዓ.ም. (ሚያዝያ 2, 2026)

የይሖዋ ምሥክሮች በየዓመቱ የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ ያከብራሉ፤ ይህም ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሎ ባዘዘው መሠረት ነው፦ “ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት።”—ሉቃስ 22:19

በዚህ ፕሮግራም ላይ ከቤተሰብህ ጋር እንድትገኝ በአክብሮት ጋብዘንሃል።

ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች

ማን መገኘት ይችላል?

ለሁሉም ሰው ክፍት ነው። ከነቤተሰብህ ጋብዘንሃል።

ፕሮግራሙ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

አንድ ሰዓት ገደማ።

ፕሮግራሙ የሚካሄደው የት ነው?

በአካባቢህ ስለሚካሄድበት ቦታ መረጃ እንዲሰጡህ የይሖዋ ምሥክሮችን አነጋግር።

ፕሮግራሙ ላይ ለመገኘት የሚጠየቅ ክፍያ ወይም ሌላ ዓይነት ግዴታ አለ?

የለም።

ሙዳየ ምጽዋት ይዞራል?

አይዞርም። በየትኛውም ስብሰባችን ላይ ቢሆን ሙዳየ ምጽዋት አናዞርም።—ማቴዎስ 10:8

የአለባበስ ፕሮቶኮል አለው?

የለውም። ይሁንና የይሖዋ ምሥክሮች ይህ የተቀደሰ ፕሮግራም ያለውን ክብር በሚመጥን መንገድ ለመልበስ ጥረት ያደርጋሉ።

በመታሰቢያው በዓል ላይ ምን ይከናወናል?

በስብሰባው መጀመሪያና መደምደሚያ ላይ ተሰብሳቢዎች መዝሙር ይዘምራሉ፤ እንዲሁም አንድ የይሖዋ ምሥክር አገልጋይ ጸሎት ያቀርባል። ፕሮግራሙ ንግግርም ያካተተ ነው፤ ንግግሩ ኢየሱስ የሞተው ለምን እንደሆነ እንዲሁም አምላክና ክርስቶስ ያደረጉልን ነገር ምን ጥቅም እንደሚያስገኝልን ያብራራል።

መጪዎቹ የመታሰቢያው በዓላት የሚከበሩት መቼ ነው?

2018 ዓ.ም. (2026)፦ ሐሙስ፣ መጋቢት 24 (ሚያዝያ 2)

2019 ዓ.ም. (2027)፦ ሰኞ፣ መጋቢት 13 (መጋቢት 22)