በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው

በሰፊው የሚታወቁ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችንና አባባሎችን ትክክለኛ ትርጉም እንድታነብ እንጋብዝሃለን። የጥቅሶቹን አውድ በማጤን ጥቅሶቹ የተጻፉበትን ዓላማ ማወቅ ትችላለህ። ተጨማሪ ማብራሪያ የሚሰጡት የግርጌ ማስታወሻዎችና ማጣቀሻዎች ግንዛቤህን ለማስፋት ይረዱሃል።

የዘፍጥረት 1:1 ማብራሪያ—“በመጀመሪያ አምላክ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ”

የመጽሐፍ ቅዱስ መክፈቻ የሆነው ይህ ጥቅስ የትኞቹን ሁለት ወሳኝ እውነቶች ይዟል?

የዘፀአት 20:12 ማብራሪያ—“አባትህንና እናትህን አክብር”

አምላክ ይህን ትእዛዝ የሚፈጽሙ ሰዎች ዕድሜያቸው እንደሚረዝም ቃል ገብቷል፤ ይህም ትእዛዙን ለመፈጸም የሚያነሳሳ ተጨማሪ ምክንያት ይሆናል።

የኢያሱ 1:9 ማብራሪያ—“ጽና፣ አይዞህ”

ተፈታታኝ ሁኔታዎችና የሚታለፉ የማይመስሉ እንቅፋቶች ሲያጋጥሙህ ድፍረትና ጥንካሬ ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

የመዝሙር 23:4 ማብራሪያ—“በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ”

የአምላክ አገልጋዮች እንደ ድቅድቅ ጨለማ ያለ ችግር በሚያጋጥማቸው ጊዜም እንኳ የአምላክን እንክብካቤ የሚያዩት እንዴት ነው?

የምሳሌ 3:5, 6 ማብራሪያ—“በገዛ ራስህ ማስተዋል አትመካ”

ከራስህ ይልቅ በአምላክ እንደምትታመን ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

የኢሳይያስ 41:10 ማብራሪያ—“እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ”

ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹን እንደሚደግፍ ለማረጋገጥ ሦስት አገላለጾችን ተጠቅሟል።

የኢሳይያስ 42:8 ማብራሪያ—“እኔ እግዚአብሔር ነኝ”

አምላክ ለራሱ ያወጣው ስም ማን ነው?

የኤርምያስ 29:11 ማብራሪያ—“ለእናንተ ያለኝን ዕቅድ እኔ ዐውቃለሁ”

አምላክ ለእያንዳንዱ ሰው የተወሰነ ዕቅድ አለው?

የማቴዎስ 6:33 ማብራሪያ—“ከሁሉ አስቀድማችሁ የአምላክን መንግሥት . . . ፈልጉ”

ኢየሱስ ይህን ሲል ክርስቲያኖች መተዳደሪያ ለማግኘት መሥራት እንደማያስፈልጋቸው መናገሩ ነው?

የማቴዎስ 6:34 ማብራሪያ—‘ስለ ነገ አትጨነቁ’

ማቴዎስ 6:34 በአዲስ ዓለም ትርጉምና በአዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ እንዴት እንደተተረጎመ አንብብ፤ እንዲሁም ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የጥቅሱን አውድና ማጣቀሻዎቹን ተመልከት። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ምን ትርጉም እንዳለው መርምር።

የማርቆስ 1:15 ማብራሪያ—“የአምላክ መንግሥት ቀርቧል”

ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት በዚያ ጊዜ መግዛት እንደጀመረ መናገሩ ነበር

የዮሐንስ 1:1 ማብራሪያ—“በመጀመሪያ ቃል ነበረ”

ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት ስላሳለፈው ሕይወት መረጃ ይሰጠናል።

የዮሐንስ 3:16 ማብራሪያ—“ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና”

ይሖዋ አምላክ እያንዳንዳችንን እንደሚወደንና የዘላለም ሕይወት እንድናገኝ እንደሚፈልግ ያሳየው እንዴት ነው?

የሮም 10:13 ማብራሪያ—“የጌታን ስም የሚጠራ”

አምላክ ብሔር፣ ጎሳ ወይም የኑሮ ደረጃ ሳይለይ ለሁሉም ሰዎች መዳን የሚችሉበትና የዘላለም ሕይወት የሚያገኙበት አጋጣሚ ከፍቷል።

የሮም 12:2 ማብራሪያ—“በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ”

አምላክ ሰዎች ለውጥ እንዲያደርጉ ያስገድዳል?

የፊልጵስዩስ 4:6, 7 ማብራሪያ—“ስለ ምንም ነገር አትጨነቁ”

የአምላክ አገልጋዮች፣ ከጭንቀታቸው እፎይ እንዲሉና ውስጣዊ ሰላም እንዲያገኙ የሚረዷቸው የጸሎት ዓይነቶች የትኞቹ ናቸው?