በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥያቄ 1

አምላክ ማን ነው?

 “ስምህ ይሖዋ የሆነው አንተ፣ አዎ፣ አንተ ብቻ በመላው ምድር ላይ ልዑል እንደሆንክ ሰዎች ይወቁ።”

መዝሙር 83:18

 “ይሖዋ፣ አምላክ መሆኑን እወቁ። የሠራን እሱ ነው፤ እኛም የእሱ ንብረት ነን።”

መዝሙር 100:3

 “እኔ ይሖዋ ነኝ። ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፣ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።”

ኢሳይያስ 42:8

 “የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”

ሮም 10:13

 “እያንዳንዱ ቤት ሠሪ እንዳለው የታወቀ ነው፤ ሁሉን ነገር የሠራው ግን አምላክ ነው።”

ዕብራውያን 3:4

 ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንስታችሁ ተመልከቱ። እነዚህን ነገሮች የፈጠረ ማን ነው? እንደ ሠራዊት በቁጥር የሚመራቸው እሱ ነው፤ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል። ገደብ ከሌለው ብርቱ ጉልበቱና ከሚያስደምመው ኃይሉ የተነሳ አንዳቸውም አይጎድሉም።”

ኢሳይያስ 40:26