መዝሙር 100:1-5
የምስጋና ማህሌት።
100 ምድር ሁሉ፣ በድል አድራጊነት ለይሖዋ እልል በሉ።+
2 ይሖዋን በደስታ አገልግሉት።+
በእልልታ ወደ ፊቱ ቅረቡ።
3 ይሖዋ፣ አምላክ መሆኑን እወቁ።*+
የሠራን እሱ ነው፤ እኛም የእሱ ንብረት ነን።*+
እኛ ሕዝቡና የማሰማሪያው በጎች ነን።+
4 በምስጋና ወደ በሮቹ፣በውዳሴም ወደ ቅጥር ግቢዎቹ ግቡ።+
ምስጋና አቅርቡለት፤ ስሙንም አወድሱ።+
5 ይሖዋ ጥሩ ነውና፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም፣ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል።+