መዝሙር 83:1-18
መዝሙር። የአሳፍ+ ማህሌት።
83 አምላክ ሆይ፣ ዝም አትበል፤+አምላክ ሆይ፣ ጸጥ አትበል፤* ደግሞም ጭጭ አትበል።
2 እነሆ፣ ጠላቶችህ እየደነፉ ነውና፤+አንተን የሚጠሉ በእብሪት ይመላለሳሉ።*
3 በስውር በሕዝቦችህ ላይ የተንኮል ሴራ ይሸርባሉ፤በውድ አገልጋዮችህ* ላይ ይዶልታሉ።
4 “የእስራኤል ስም ተረስቶ እንዲቀር፣ኑ፣ ሕዝቡን እንደምስስ” ይላሉ።+
5 የጋራ ዕቅድ ይነድፋሉ፤*በአንተ ላይ ግንባር ፈጥረዋል፤*+
6 የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣ ሞዓብና+ አጋራውያን፣+
7 ጌባል፣ አሞንና+ አማሌቅ፣እንዲሁም ፍልስጤም+ ከጢሮስ ነዋሪዎች+ ጋር አበሩ።
8 አሦርም+ ከእነሱ ጋር ተባብሯል፤ለሎጥ ልጆችም+ድጋፍ ይሰጣሉ።* (ሴላ)
9 በምድያም እንዳደረግከው፣በቂሾንም ጅረት* በሲሳራና በያቢን ላይ እንዳደረግከው አድርግባቸው።+
10 እነሱ በኤንዶር+ ተደመሰሱ፤ለምድርም ፍግ ሆኑ።
11 በመካከላቸው ያሉትን ታላላቅ ሰዎች እንደ ኦሬብና ዜብ፣+አለቆቻቸውንም* እንደ ዘባህና ጻልሙና አድርጋቸው፤+
12 እነሱ “አምላክ የሚኖርባቸውን ቦታዎች እንውረስ” ብለዋልና።
13 አምላኬ ሆይ፣ ነፋስ እያሽከረከረ እንደሚወስደው ኮሸሽላ፣*+ነፋስ እንደሚጠርገው ገለባ አድርጋቸው።
14 ጫካን እንደሚያቃጥል እሳት፣ተራሮችን እንደሚያነድ ነበልባል፣+
15 አንተም እንዲሁ በሞገድህ አሳዳቸው፤+በአውሎ ነፋስህም አሸብራቸው።+
16 ይሖዋ ሆይ፣ ስምህን ይሹ ዘንድ፣ፊታቸውን በኀፍረት ሸፍን።*
17 ለዘላለም ይፈሩ፣ ይሸበሩም፤ውርደት ይከናነቡ፤ ደግሞም ይጥፉ፤
18 ስምህ ይሖዋ የሆነው አንተ፣+አዎ፣ አንተ ብቻ በመላው ምድር ላይ ልዑል እንደሆንክ+ ሰዎች ይወቁ።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ዱዳ አትሁን።”
^ ወይም “ራሳቸውን ቀና ያደርጋሉ።”
^ ቃል በቃል “በሸሸግካቸው።”
^ ወይም “ቃል ኪዳን ተጋብተዋል።”
^ ቃል በቃል “በአንድ ልብ ይማከራሉ።”
^ ቃል በቃል “ክንድ ሆኑ።”
^ ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
^ ወይም “መሪዎቻቸውንም።”
^ ወይም “አረም።”
^ ቃል በቃል “ሙላው።”