ለሮም ሰዎች የተጻፈ ደብዳቤ 10:1-21

  • መጽደቅ የሚቻልበት መንገድ (1-15)

    • እምነትን በይፋ መናገር (10)

    • “የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል” (13)

    • ያማሩ እግሮች ያሏቸው ሰባኪዎች (15)

  • ምሥራቹን አንቀበልም አሉ (16-21)

10  ወንድሞች፣ ለእስራኤላውያን ከልቤ የምመኘውና ስለ እነሱ ለአምላክ ምልጃ የማቀርበው እንዲድኑ ነው።+ 2  ለአምላክ ቅንዓት እንዳላቸው እመሠክርላቸዋለሁና፤+ ሆኖም ቅንዓታቸው በትክክለኛ እውቀት ላይ የተመሠረተ አይደለም። 3  የአምላክን ጽድቅ ሳያውቁ+ የራሳቸውን ጽድቅ ለመመሥረት+ ስለፈለጉ ራሳቸውን ለአምላክ ጽድቅ አላስገዙም።+ 4  የሚያምን* ሁሉ መጽደቅ ይችል ዘንድ+ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።+ 5  ሙሴ በሕጉ አማካኝነት ስለሚገኘው ጽድቅ ሲገልጽ “እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት ይኖራል” ሲል ጽፏል።+ 6  ሆኖም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ በተመለከተ እንዲህ ተብሏል፦ “በልብህ+ ‘ወደ ሰማይ ማን ይወጣል?’ አትበል፤+ ይህም ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ 7  ወይም ‘ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል?’ አትበል፤+ ይህም ክርስቶስን ከሞት ለማስነሳት ነው።” 8  ይሁንና ቅዱስ መጽሐፉ ምን ይላል? “ቃሉ ለአንተ ቅርብ ነው፤ ደግሞም በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው”፤+ ይህም እኛ የምንሰብከው የእምነት “ቃል” ነው። 9  ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ በይፋ ብትናገር+ እንዲሁም አምላክ ከሞት እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህና። 10  ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና፤ በአፉ ደግሞ እምነቱን በይፋ ተናግሮ ይድናል።+ 11  ቅዱስ መጽሐፉ “በእሱ ላይ እምነት የሚጥል ሁሉ አያፍርም” ይላል።+ 12  በአይሁዳዊና በግሪካዊ መካከል ምንም ልዩነት የለምና።+ የሁሉም ጌታ አንድ ነው፤ እሱም የሚለምኑትን ሁሉ አብዝቶ ይባርካል።* 13  “የይሖዋን* ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።”+ 14  ይሁንና ካላመኑበት እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ስለ እሱ ሳይሰሙስ እንዴት ያምኑበታል? ደግሞስ የሚሰብክላቸው ሳይኖር እንዴት ይሰማሉ? 15  ካልተላኩስ እንዴት ይሰብካሉ?+ ይህም “የተሻለ ነገር እንደሚመጣ ምሥራች የሚናገሩ ሰዎች እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው!”+ ተብሎ እንደተጻፈው ነው። 16  ሆኖም ምሥራቹን የታዘዙት ሁሉም አይደሉም። ኢሳይያስ “ይሖዋ* ሆይ፣ ከእኛ የሰማውን* ነገር ያመነ ማን ነው?” ብሏልና።+ 17  ስለዚህ እምነት የሚገኘው ቃሉን ከመስማት ነው።+ ቃሉን መስማት የሚቻለው ደግሞ ስለ ክርስቶስ የሚናገር ሰው ሲኖር ነው። 18  ይሁንና ‘ሳይሰሙ ቀርተው ይሆን?’ ብዬ እጠይቃለሁ። በእርግጥ ሰምተዋል፤ “ጩኸታቸው ወደ መላው ምድር ወጣ፤ መልእክታቸውም እስከ ዓለም ዳርቻዎች ተሰማ” ተብሏልና።+ 19  ይሁንና ‘እስራኤላውያን ሳያውቁ ቀርተው ይሆን?’ ብዬ እጠይቃለሁ።+ ሙሴ አስቀድሞ “እናንተን፣ ሕዝብ ባልሆኑት አስቀናችኋለሁ፤ ሞኝ በሆነ ብሔር አማካኝነትም ክፉኛ አስቆጣችኋለሁ” ብሏል።+ 20  ኢሳይያስም በድፍረት “ያልፈለጉኝ ሰዎች አገኙኝ፤+ እኔን ለማግኘት ባልጠየቁ ሰዎችም ዘንድ የታወቅኩ ሆንኩ” ብሏል።+ 21  እስራኤልን በተመለከተ ግን “ወደማይታዘዝና ልበ ደንዳና ወደሆነ ሕዝብ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ” ብሏል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “እምነቱን በተግባር የሚያሳይ።”
ወይም “እሱም ለሚለምኑት ሁሉ በልግስና ይሰጣል።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “እኛ የተናገርነውን።”